ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ (ከታማኝ በየነ እና ሲሳይ አጌና)
ለአቶ ጌታቸው አሰፋ
ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ
ስማችን ከስር የተመለከተው ግለሰቦች በሃገራችን ነጻነት እውን እንዲሆን ከሚፈልጉ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያን ውስጥ እንገኛለን። በሃገራችን በነጻነት መኖር ወይንም ሃገራችንን በነጻነት ማየት ባንችልም በሰው ሃገር በነጻነት እንኖራለን፥ ሆኖም በሃገራችን ያጣነውን ነጻነታችንን ለማስመለስ፣ በጥቅል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንም በነጻነት እንዲኖሩ የአቅማቸውን ጥረት ከሚያደርጉት ውስጥ ነን።ይህ ጥረታችን በደህንነት መስሪያ ቤትዎም ሆነ በሕወሀት መንግስት እንደማይወደድ የምናውቅ ቢሆንም ማስፈራሪያና መደለያ በማቅረብ ትደፍሩናላችሁ የሚል ግምት ግን አልነበረንም።
ለዚህ መነሻ የሆነን እና ከስራ ባልደርቦቻችን እንዲሁም ካለንበት ተቋም ኢሳት ውጭ በግል ለመጻፍ ያነሳሳን ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም /June 29/2016/ የተላከልን መልዕክት ነው።የርሶ ማለትም የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች እንዲሁም የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በየወላጆቻችን ቤት በመገኘትና በመጥራት በተጠቀሰው ቀን የሰጡት ማሳሰቢያ እና መደለያ እንደደረሰን እየገለጽን፣ እ ንደማንቀበል ለማረጋገጥ ይህን ለመጻፍ ተገደናል ።
ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ ወይንም ቡድን ቢሆን እንኳን ወንጀል በስጋ ዝምድና እንደማይተላለፍ ለአቅም አዳም ለደረሱ ያውም መንግስታዊ ሃላፊነት ላይ ላሉ ባለስልጣናት እንደማይጠፋቸው ቢታምንም በክፋት፣በጥላቻ እና በዘረፋ ግዚያቸውን ለሚያባክኑት የሕወሓት መሪዎች ይህ አለመከሰቱ አይገርመንም። እኛን ዝም ለማሰኘት አዛውንት እና ሕጻናትን በመያዣነት /hostages/ ለመያዝ ስትወስኑ ምን ያህል አቅም እያነሳችሁና ተስፋ እየቆረጣችሁ እንድሆንም አሳይቶናል።
እናንተ በደል አንገፈገፈን ብላችሁ ለመብታችሁ እሰከመጨረሻው ታግላቹኋል።እናንተ በተራችሁ በበደል ላይ በደል ስትጭኑብን ፡ ኢትዮጵያን በዘረኝነት ስትቀጠቅጡና ስትዘርፉ፣ ዜጎችን በገዛ ሃገራቸው ባይተዋር ስታደርጉ ይህንን በዝምታ እንድንመለከት ማስፈራሪያ እና መደለያ መላካችሁ የሚያናድድ ቢሆንም፣ ይህ ድፍረት ይበልጥ ጉልበት እንደሰጠን ለርስዎም ሆነ በሕወሃት ለሚመራው መንግስት ማስታወስ እንሻለን። ማናቸውም ማሰፈራሪያና መደለያ እንዲሁም ቤተሰቦቻችንን በዕገታ መያዝ ከነጻነት ጉዞ አንዲት ስንዝር እንደማትመልሱን በተግባራዊ ርምጃዎቻችን የምትመለከቱት ይሆናል።
ታማኝ በየነ እና ሲሳይ አጌና

Show More Reactions
No comments:
Post a Comment