Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, July 16, 2016

የእስራኤል የደህንነት ሠራተኞች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በፈሳሽ ኬሚካል እንዲታጠቡ አስገደዱ



የእስራኤል የደህንነት ሠራተኞች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በፈሳሽ ኬሚካል እንዲታጠቡ አስገደዱ
========
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁን ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ወደሀገር ውስጥ የመጡት የእስራኤል የደህንነት ሠራተኞች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በፈሳሽ ኬሚካል እጃቸውን እንዲታጠቡ አስገደዱ።
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በሸራተን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት በተካሄደው የቢዝነስ ፎረም ላይ ተካፋይ ለመሆን በተደረገላቸው ጥሪ የተገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከእሥራኤል የደህንነት ሠራተኞች በቀረበላቸው ፈሳሽ ንጥረ ነገር እጃቸውን እንዲታጠቡ፣ ከኮምፒውተር ጋር የሚናበብ ሰዓት መሰል ፕላስቲክ እጃቸው ላይ እንዲያጠልቁ መገደዳቸውን የሰንደቅ ጋዜጣ ምንጮች አረጋግጠዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የደህንነት ባለሙያ በሰጡን ማብራሪያ፣ “ይህ አይነቱ የሴኩሪቲ ፍተሻ ኔጌቲቭ ሊስት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሁሉንም የስብሰባ ተካፋዮች በአንድ አይነት መንገድ በመመደብ የሚደረግ ነው። ለየትኛውም ተሳታፊ የተለየ ፍተሻ ሳይቀመጥ ሁሉንም እንደተጠርጣሪ ወስዶ የሚደረግ ፍተሻ ነው።” ብለዋል።
አያይዘውም፣ በደህንነት በአብዛኛው ፈሳሽ ኬሚካል የሚጠቀሙት ምንአልባት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ተጋባዥ እንግዶችን በሚጨብጡ ሰዓት በአንዳንድ ሰዎች የተለየ ተልዕኮ ሰውነታቸው የሚመርዝ ነገር እንዳይተላለፍ ለመጠንቀቅ ነው። የደህንነት ጥበቃው በኢትዮጵያ ብዙም ያልተለመደ የደህንነት አሰራር በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ቢደናገጡ ብዙ አያስገርምም ብለዋል።
Source Sendek Newspaper

No comments:

Post a Comment

wanted officials