Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 11, 2016

የሐብታሙ አያሌው እህት ጥሪ አቀረበች



የሐብታሙ አያሌው እህት ጥሪ አቀረበች
============
ወይንሸት አያሌው እባላለሁ የሐብታሙ አያሌው እህት ነኝ፡፡በአሁኑ ሰዓት ወንድሜ ሐብታሙ ታሞ ህይወቱ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ህይወቱን ለማዳን ወደ ውጪ አገር ሄዶ መታከም ያለው የመጨረሻው አማራጭ ቢሆንም ለሰው ልጅ መብትና ህይወት ግድ የማይሰጣቸው የአገር ገዢዎች የፖለቲካ አመለካከቱን ስለማይወዱት ብቻ በተለመደው የጭካኔ አሰራራቸው ቀጥለውበት ትናንት በእስር ቤት አኑረውት ያሰቃዩት አልበቃ ብሏቸው ከሰው ልጅ በማይጠበቅ ጭካኔ እየተሳለቁበት ይገኛሉ፡፡
ሐብታሙ የሚገኝበትን ስቃይ አይተውና ሰምተው እንዳላዩና እንዳልሰሙ በመሆን ሞቱን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡መላው ህዝብ ሐብታሙ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ የጣሉበትን የጉዞ ማዕቀብ እንዲያነሱለት የጮህውን ጩህት በማን አለብኝነት ስቃዩን የሚያራዝም ምክንያት እየፈጠሩ የብዙዎችን ጮህት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለውታል፡፡
የሐብታሙን ስቃይ እንደ መንፈስ እርካታ መመልከታቸውን በማቆም ወደህሊናቸው እንዲመለሱና በሐብታሙ፣በባለቤቱ፣በህጻን ልጁና በቤተሰቡ ጫማ ራሳቸውን በማስገባት ከዚህ በላይ እንዳይጨክኑበት ለመጠየቅ እወዳለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials