Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 26, 2016

በሰሜን ጎንደር በወያኔና በአማራ ሕዝብ መካከል ፍጥጫው እየተባባሰ ነው፥






በመሃል ኢትዮጵያ፥ በአርሲ፥ በባሌ፥ በሓረር እና በቦረና የኦሮሞ ወጣት ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ላይ ነው፥ በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለወንበዴ መንግሥት አንገዛም ባይነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
================================================
ሕዝበ ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር ለለውጥ ተንቀሳቅሷል።
ዘረኛው የወኔ መንግሥትም በበኩሉ ሕዝብ ማሸበሩንና ሰላማዊ ዜጎችን ማዋከቡን ተያይዞታል፥
ከሰሜን ጎንደር ወደ መሃል ኢትዮጵያ ኦሮምያ እና ወደ ደቡቡ ኢትዮጵያ የትግሉ ግለት እየተዛመተ፥ የለውጥ እሳት በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ነው።
ጀግናው የኦሮሞ ልጅና ጀግናው አማራ ሕዝብ፥ የፋሺስት ወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለው በደል በቃ በማለት፥ ዘርና ኃይማኖት ሳይለየው በአንድነት ሊታገል፥ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር መቃብር ላይ የነጻነት ችቦ ሊያበራ ቆርጦ ተነስቷል።
በኦሮሞ ሕዝብ የተጀመረው የመረረ አንገዛም ባይነት ጎንደር ላይ ወደ ለየለት ፍልሚያ ተቀይሮ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ የወያኔን ዙፋን እያንቀጠቀጠው ይገኛል፥
ኢትዮጵያውያን ለአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከእያቅጣጫው የትግል ጥሪ እያቀረቡ ነው፥ ጠላት ወያኔን አቅፎ፣ ደግፎና፣ ሸፋፍኖ የያዘው የአዲስ አበባ ነዋሪ፥ ወጣቱ፣ ተማሪውና ወዛደሩ ተባብሮ አራት ኪሎ ላይ የተንሰራፋውን የወያኔ መንግሥት ገልብጦ በመጣል ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ያስተላልፋሉ፥
ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

No comments:

Post a Comment

wanted officials