Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 15, 2016

የዘር ማጥፋት ዘመቻን ለማውገዝ የተጠራ አስቸኳይ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!



የዘር ማጥፋት ዘመቻን ለማውገዝ የተጠራ አስቸኳይ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!
በአማራ ጥላቻ ተወልዶ ያደገው ወያኔ በመጨረሻ የጥፋት ዘመኑ አማራውን ከኢትዮጵያ ምድር የማጥፋት ዘመቻውን በጎንደር ህዝብ ላይ ጀምሯል። ወልቃይትን በግድ ትግሬ ነህ በሚል ለ25 አመታት የሰራው ግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ህዝቡ ማንነቱን ለማስከበር የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል።
የወያኔ የጥላቻ ልክፍትና አልጠግብ ባይነት ዜጎች ከሚኖሩበት ቀዬ በማፈናቀል በኦሮሚያ፣ በጋንቤላ፣ በሱማሌ፣ በአፋር፣ በቅማንት፣ በአዲስ አበባ በሌሎችም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶችን፣አዛውንቶችን፣ እመጫትን፣ እርጉዝ ሴትንና ህጻናትን ሳይል በጅምላ በመጨፍጨፍ ቀሪዎችንም በእስር ቤት አጉሯል።
አሁንም ይሄንን ድርጊቱን ለመቀጠል ማህበራዊ መገናኛዎችን በመዝጋት በከፍተኛ ቁጥር የጦር ሀይሉን በጎንደር ህዝብ ላይ በማሰማራት ያቀደውን የዘር ፍጅት ለማጋለጥ እና ይሄንንም ለማድረግ የሚረዱትን መንግስታት ለመቃወም እንዲሁም ከህዝባችን ጎን መቆማችንን ለማሳየት በተጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት ወገናዊነቶን እንዲያሳዩ ተጋብዘዋል።
ቦታ ፦ Department of State
2201 C St NW
Washington, DC. 20520
ቀን ፦ ሰኞ July 18, 2016
ሰአት ፦ 9:00 AM
አዘጋጅ ፦ የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል

No comments:

Post a Comment

wanted officials