Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 3, 2016

ለጵጵስና የተጠቆሙት አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ: ከኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ በዝሙት ቅሌት የተባረሩ ያሉ መናፍቅ ናቸው

ለጵጵስና የተጠቆሙት አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ: ከኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ በዝሙት ቅሌት የተባረሩ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በጌታ ሳያምን በውኃ ይጋፋል” ያሉ መናፍቅ ናቸው!


Melake Selam Aba Kale Tsedik Mulugeta
  • በተማሪነቱ፣ የመናፍቅነት ጠባይ እና ዝንባሌ በማሳየት፣ በደቀ መዛሙርት ማስረጃ ቀርቦበታል
  • ከምእመናን ያለደረሰኝ የሰበሰበውን 10ሺሕ ዶላር፣ ለምን እንዳዋለው ሳይታወቅ ተጠቅሞበታል
  • በ3ሺሕ500 ዶላር ለተዋዋለበት ሥራ 500 ዶላር በመክፈል እምነት አጉድሏል፤ አደራ በልቷል
  • መናፍቅነቱ፣ ጥቅመኛነቱ እና ሴሰኛነቱ፤ በሔደባቸው ስቴቶች ኹሉ መጠጊያ ሲያሳጣው ኖሯል
*               *               *
  • “ሴትን ለግላዊ ሥጋዊ ጥቅም ብቻ መገልገል” በሚሰኝ “sadistic” ፍትወቱና ግብሩ ይታወቃል
  • ጋለሞታዎችን አሳዳጅ ነው፤ባለትዳር ሴቶችንም በማማገጥ ለቤተሰብ መፍረስ መንሥኤ ኾኗል
  • የቤቱ፣ የሆቴልና የሞቴል ቅንዝረኛነቱ ሳይበቃ በቤተ ክርስቲያን ቢሮና ማረፊያም አይታቀብም
  • የኦክላንድ ምእመናን፣ ለሴት ሕፃናትና አዳጊዎቻቸው የሚሰጉት ጉምዡና ሴሰኛ ኾኖ ቆይቷል
*               *               *
  • የዝሙት ቅሌቱ በምስክሮች፣ በፎቶና በቪዲዮ ማስረጃዎች ተረጋግጦ ከቤተ ክርስቲያን ተባሯል
  • በፓትርያርኩ ወዳጅ አግባቢነት ወደ ሀገር ተመልሶ የጠቅ/ጽ/ቤት የውጭ ጉዳይ ሓላፊ ኾኗል
  • የውጭ ግንኙነት ጉዳዮችን፣ የእናት ቤተ ክርስቲያንን አንድነት በሚጎዳ መልኩ እየመራ ይገኛል
  • ቅ/ሲኖዶስ ከሓላፊነቱ እንዲነሣ ቢወስንም፤ ለማዕርገ ጵጵስና ተጠቁሞ ወደ ግቡ እየተዳረሰ ነው
*               *               *
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ክፍት በኾኑ የአህጉረ ስብከት መንበረ ጵጵስናዎች ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጦ ለመሾም በወሰነው መሠረት፣ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት አስመራጭ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በሰብሳቢነት፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጸሐፊነት የሚመሩትና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በአባልነት የሚገኙበት ኮሚቴው፣ እስከ አኹን ድረስ ባለው መረጃ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ የተጠቆሙ በትንሹ ከ74 ያላነሱ ቆሞሳትንና መነኰሳትን ስም ዝርዝር መሰብሰቡ ተገልጧል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በማስፈጸሚ ደንቡ መሠረት፣ የሐዲሳን ኤጲስ ቆጶሳት ሢመቱ፥ የጥቆማ፣ የጥናትና ምርምራ እንዲኹም የዕጩ ምርጫ የተሰኙ ሦስት ደረጃዎች አሉት፡፡ ጥቆማዎችን ሲቀበልና ሲመዘግብ የቆየው ኮሚቴው፣ በሳምንቱ መጨረሻ በምዘናና ምርመራ ማጣራት የሚጀምር ሲኾን፤ ይህም ለምርጫ የሚቀርቡ ከ28 እስከ 30 ዕጩዎችን ለመለየት እንደሚያስችለው ተጠቅሷል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው የማጣራቱን ውጤት እስከ ሰኔ 30 ቀን እንዲያቀርብ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተገለጸ ቢኾንም፤ ከተጠቋሚዎች ብዛትና ለምርመራው የሚያስፈልጉ በቂ ማስረጃዎችን ከማግኘት አኳያ ቀነ ገደቡ ሊራዘም እንደሚችል ተሰምቷል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ በይሁዳ ቦታ ሌላ ሐዋርያ ለመተካት ከጸሎትና ዕጣ በፊት ምርጫ እንዳደረጉት ኹሉ፤ በማስተማር፣ በማስተዳደርና ሥርዓተ አምልኮን በመምራት በዋና መሪነት የሚያገለግልን ኤጲስ ቆጶስ ለመምረጥም፣ በማስፈጸሚያ ደንቡ የተቀመጡት መስፈርቶች በከፊል እንኳ ስለመሟላታቸው በወጉ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ኮሚቴው በከፍተኛ መመዘኛነት የያዛቸው፡- የተጠቋሚው የእምነት አቋምና የትምህርት ዝግጅቱ፤ የአገልግሎትና የአስተዳደር ብቃቱ፤ ሥነ ምግባሩና በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እንዲኹም በራስ አገዝ ልማት ያስመዘገባቸውን የሥራ ፍሬዎች ተኣማኒነትና ተቀባይነት ባለው መልኩ ሰብስቦና ቀምሮ ለማጥናት በርግጥም የተረጋጋና የተቀናጀ አካሔድ የሚጠይቅ ነው፡፡
ይኹንና መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ አስመራጭ ኮሚቴው፣ በአንድ በኩል፣ ከተጠቆሙት መካከል ጥቂት በማይባሉት ቆሞሳትና መነኰሳት አስጊና አስነዋሪ ማንነት በአዘኑና በተደናገጡ ምእመናን ስሞታና አቤቱታ ሲጨነቅ፤ በሌላ በኩል፣ “በብፁዕነትዎ ጸሎት ነው ለዚኽ የደረስኩት፤ አኹንም ዕድሉ እንዳያልፈኝ አስቡኝ፤ አትርሱኝ” በሚሉ ሲሞናውያን-የሹመት ፍቅረኞችና-ባለተስፋዎች፡- ውዳሴ ከንቱ፣ እጅ መንሻ/ቡራኬ ወይም ገጸ በረከት በሚሉት/ እንዲኹም እስከ ሀገረ ስብከት በሚላኩ የባለሥልጣናትና የተደራጁ ግለሰቦች የስልክና የአካል አማላጅነትና ደጅ ጥናት እየተዋከበ እንዳለ በስፋት ይነገራል፡፡
በዓምባገነንነታቸው ከመቀጣት አልፎ ከተለያዩ ሴቶች ጋር በፈጸሙት የዝሙት ነውር ጉዳያቸው የመብት ተሟጋች አካላት ዘንድ እና ፍ/ቤት የደረሰው፣ እንደ አባ ዕንቁ ሥላሴ ተረፈ(የአ/አበባ ካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል አለቃ) ያሉቱ፤ በምዝበራና በፀረ ልማት አካሔድ ማኅበረ ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤቶችን ያስመረሩቱም፤ “ደስ ብሎኛል፤ ደስ ይበላችኹ፤ የደብራችኹ አስተዳዳሪ ለጵጵስና ሊመረጡ ነው!” እያሉ በሰንበትና በክብረ በዓላት በዐውደ ምሕረት እያስለፈፉ በሚመሩት ምእመን ላይ ማላገጥ ይዘዋል፤ እንደሚባለው ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ በተካኑበት ድለላም፣ ረብጣ ብር በማቀባበል በሲሞናዊነት መንገድ የሹመት ፍልሚያና ፍጅቱን ማጧጧፋቸው የከተማው ወሬ ኾኗል፡፡
እውነቱ ግን÷ የት እንደተማሩ፤ ምን እንደሠሩ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የቸገራቸውና በመስፈርቱ መሠረት “ዜሮ ናቸው”መባላቸው ነው፡፡ አንዳንድ ብፁዓን አባቶችንም፣ “ወይ መስፈርቱ ወይ ሰዎቹ መሻሻል አለባቸው” ማሰኘታቸው ነው፡፡ ከተጠቋሚዎቹ÷ በእውነት “መላእክት እንኳ ይመሰክሩላቸዋል” የተባሉትን ገዳማውያን አባቶችና የአብነት መምህራን የማይጨምረው፣ ንጽሕ የመጠበቅ ጉዳይ፣ ብዙዎቹ የተፈተኑበት ቢኾንም፤ የአንዳንዶቹ ግን “ምንኵስና ትርጉሙ ተለወጠ ወይ? ድንግልና፣ መስፈርት መኾኑ ቀረ ወይ?”እስኪባል ድረስ ከፍተኛ ቁጣ እንደቀሰቀሰ ካህናትና ምእመናን ከሚያደርሷቸው ማስረጃዎች ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በአሜሪካ ካሊፎርንያ ስቴት የኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ ምእመናን፣ ሰሞኑን ለጡመራ መድረኩ የማያወላፍት ማስረጃ አድርሰዋል፡፡ ማስረጃው፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊውን መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ አራጋውንየሚመለከት ሲኾን፤ ለኤጲስ ቆጶስነት ከተጠቆሙት ቆሞሳት መግባታቸው ያስነሣውን ተቃውሞ መነሻ ያደረገ ነው፡፡Continental Lodge
Aba Kale Tsidek going out from Continental Lodge02
እ.አ.አ ኦገስት 6 ቀን 2013፤ ከጠዋቱ 1 ከ02 ደቂቃ፤ አንድ ፖሊስና ሰባት የኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በምስክርነት የታዘቡት ትዕይንት፡- መልአከ ሰላም ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ፣ በምሥራቃዊ ኦክላንድ ከተማ 15ኛ ጎዳና ከሚገኝና ኮንትኔንታል ሎጅ ከተባለ ሞቴል ከአንዲት ባለትዳር ሴት ጋር ሌሊቱን ካሳለፉ በኋላ በሰማያዊ ጅንስ ሱሪና በስኒከር ጫማ ራሳቸውን በጃኬት (a hoody jacket) ሸፍነው ሲወጡ በቪዲዮና በፎቶ ካሜራ ተቀርፀዋል

በሰነድ፣ በቪዲዮና በፎቶ ማስረጃዎች የተደገፈው የምእመናኑ ተቃውሞ፤ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ፣ ያለሰነድ የርዳታ ገንዘብ በመሰብሰብ ለግላቸው መጠቀማቸውን፤ በዚኹ ምዝበራቸው አምነው የተጠጓቸውን ምእመናን እምነት ከማጉደላቸው ባሻገር፤ በዝሙት ቅሌት ለተቀደሰው ጋብቻ መፍረስና ለቤተሰብ መበተን መንሥኤ መኾናቸውን፤ የኖላዊነት አደራቸውን በመብላታቸውና ምንኵስናዊ ማዕርጋቸውን በማዋረዳቸው ከቤተ ክርስቲያን መባረራቸውን በመጥቀስ፣ ለከፍተኛው የክህነት ማዕርግ ሊጠቆሙ እንደማይገባ ያስረዳል፡፡
‘አባ’ ቃለ ጽድቅ፣ ዝሙትን መተዳደርያቸው ካደረጉ(call girls) እና ከባለትዳር ሴቶች ጋር፣ ከመኖርያ አፓርታማቸው፣ ከሆቴሎችና ከሞቴሎች አልፎ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር በሚገኙ ቢሮዎችና ማረፊያ ቤቶችም ሳይቀር መፈጸማቸው የአቤቱታው አሳዛኝ ክፍል ነው፡፡ የመሠረቱትን ደብርና ያመኗቸውን ማኅበረ ምእመናን በሚያሳፍር ኹኔታ፣ ሴሰኝነት መለያ ባሕርያቸው እስኪመስል ደርሶ፣ ወላጆች፣ ለሴቶች ሕፃናትና አዳጊ ልጆቻቸው ጭምር እንደሚሰጓቸው መግለጻቸው፣ የአቤቱታው አስደንጋጭና አሳሳቢ ክፍል ነው፡፡ አንድ አባት፣ “የምንሾመው ኮርማዎችን ነው ወይ?”ያሉት ማንን አይተው ይኾን?
Now knowing the facts that has surfaced and became evident, the main question which remains that no one has any way of figuring it out will be, how his behavior was towards the Sunday School Kids and Teenagers; especially, towards the young innocent teenage girls. This is the scariest part that is haunting family members who have teenagers within the congregation.
ሌላውም ማስረጃ፣ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ የሥነ ምግባር ብልሽት ብቻ ሳይኾን በእምነት አቋማቸውም፣ የመናፍቅነት ጠባይና ዝንባሌ እንዳላቸውይገልጻል፡፡ ማስረጃው፣ በቀድሞ አጠራሩ ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት፣ ለአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሚያዝያ 16 ቀን 1990 ዓ.ም. በቁጥር 787/2/10/90 የተላከ የደቀ መዛሙርት አቤቱታ ነው፡፡
St. Paul college Kale Tsidek Mulugeta
በረከታቸው ይድረሰንና፣ ዋና ዲን በነበሩት በብፁዕ አቡነ ቶማስ ተፈርሞ የወጣው ይኸው የቀናዕያን ደቀ መዛሙርት አቤቱታ፤ በጉዳዩ፣ በኑፋቄ በተጠረጠሩ ሦስት መምህራንና ስድስት ተማሪዎች ላይ ማስረጃ ለማቅረብ መኾኑን በማመልከት አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥ ይጠይቃል፡፡
St. Paul college Kale Tsidek Mulugeta2
በተ.ቁ(9) ስማቸው የተጠቀሰው አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጌታ ሳያምን በውኃ ይጋፋል በማለት ጥንታዊና ሐዋርያዊ የኾነውን ክርስቲያናዊ ትውፊታችንን እንደሚያናንቁ በአቤቱታው ገጽ 12 ላይ ሰፍሯል፡፡ በዚኽም ምእመናን የሚፈወሱበትን የቅዳሴ ጠበል ሲነቅፉ መሰማታቸው በምስክር ቃል ተረጋግጦባቸዋል፡፡ “ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችኹ”(ማቴ.7፥16) እንደተባለው፣ በሚያሳዩት የመናፍቅነት ጠባይና ልዩ ዝንባሌ የተነሣ ተገቢው ውሳኔ እንዲተላለፍባቸው ጥያቄ ቀርቦባቸው ነበር፡፡
“መጋቢት 5 ቀን 1990 ዓ.ም. በሚከበረው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ቀን በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናን፤ በውኃ ሲጋፉ አይቼ በጣም አዝኛለኹ፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ በጌታ ሳያምን በውኃ ይጋፋል፤ በማለት የቤተ ክርስቲያናችንን ትውፊት እና ምእመናን የሚፈወሱበትን የቅዳሴ ጠበል ሲነቅፉ መስማታቸውን ዲ/ን ከፍ ያለው ለማ መስክረዋል፡፡”(ገጽ 12)
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አስመራጭ ኮሚቴውን ሲሠይም፣ እንዲመረጡለትና እንደሚሾማቸው የገለጻቸው ዕጩዎች፡-
  • ፈተናውንና መሰናክሉን ኹሉ አልፈው ዕውቅና ያገኙትን፤
  • በብሔር አቀፍና በዓለም አቀፍ ትምህርት የበሰሉትን፤
  • የወቅቱን ችግር ይፈታሉ ተብሎ እምነት የተጣለባቸውንና የሚጣልባቸውን፤
  • ለተልእኮ የሚፋጠኑትን ቆሞሳት እና መነኰሳት ነው፡፡
በርግጥ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ፣ ከዘመኑ ትምህርት በአይ.ሲ.ቲ የበርክሌይ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ፤ ከአብነቱም የቅኔና ቅዳሴ ዐዋቂ እንደኾኑ ተነግሯል፤ ለፓትርያርኩም፣ “የውጭ ቋንቋ ተናጋሪ ነው፤ ይረዳዎታል” ተብለው በኒውዮርኩ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ወዳጃቸው አግባቢነት ተልኮላቸው በቀጥታ በውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ሾመዋቸዋል፡፡
ይኹንና “የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና በጌታ አላመነም” ያሰኛቸው መናፍቃዊ ጠባያቸውና ዝንባሌአቸው ግን የሚታገሡት አይደለም፤በምግባራቸውም የሚታወቁት ፈተናውንና መሰናክሉን በማለፍ ሳይኾን ጥበቃ ለሚያስፈልገው የጋብቻ እና ቤተሰባዊ ሕይወት ጠንቅ እና ትውልዳዊ ስጋት ሲኾኑ ነው፡፡
ለተልእኮ ከመፋጠን አኳያም፣ እንደ ውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊነታቸው፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሥር ኾነው ከሚሠሩት ይልቅ የፓትርያርኩን ጽ/ቤት ተገን አድርገው በቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች የሚፈጽሙት ደባ አመዝኖ ይገኛል፡፡
የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን አፈጻጸም ሳይቀር በማዘግየትና በመቀሠጥ ነው፣ መንበረ ፓትርያርኩን የተጠጉበትን ኅቡእ ዓላማ እያስፈጸሙ ያሉት፡፡ በውሳኔዎች አተገባበር የግለሰቦችን ፍላጎት በማስጠበቅ የግል ጥቅማቸውን ጭምር ያካብታሉ፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ፓትርያርኩን በጎን እያስፈረሙ በሚልኳቸው ደብዳቤዎች፣ ዕርቀ ሰላም ወርዶ ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው አንድነት እንዲጠናከር ሳይኾን ግጭትና መከፋፈል እንዲባባስ የሚያደርጉበት እኩይ ተግባራቸው በሚገባ ይታወቃል፡፡
በተለይ በጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ካቴድራል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማጣራት የተጓዘው ልኡክ አባል ኾነው ቢሔዱም፤“የደቡብ አፍሪካን ጉዳይ እንዳይኾን ያደረገው እርሱ ነው፤” ይላሉ፣ አንድ የቡድኑ ባልደረባ፡፡ በማጣራቱ ሒደት፥ አስተዳደሩን ከምእመናን፤ ምእመናንን ከምእመናን በሚለያይ አድሏዊ አቋም፣ ጠብንና ዓምባጓሮን ያበረታቱበት፤ በሪፖርቱ ዝግጅትም፣ የልኡኩ አባላት የኾኑ ብፁዓን አባቶች እንዳይግባቡና ሪፖርቱም ተቀባይነት አጥቶ አጥጋቢ መፍትሔ እንዳይገኝ የበጠበጡበት ሚናቸው ይጠቀሳል፡፡
የብዙኃን ካህናትንና ምእመናንን ተቃውሞ ችላ በማለት፣ በአሜሪካው “ተሰዳጅ ሲኖዶስ”፣ ሰሞኑን ከተሾሙት አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ ጋር፣ በዓላማ የተሳሰረና ዛሬም የቀጠለ ጥብቅ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ “ማሊያው እዚኽ ነው፤ ቡድኑ ግን እዚያ ነው፤” ይላሉ አካሔዳቸውን የነቁበት፡፡
Aba Kale Tsidek and Aba Wolde Tinsae Ayalneh
እንደ አባ ወልደ ትንሣኤ ኹሉ፣ እርሳቸውም ሳይገባቸው “ዕድሉ እንዳያልፈኝ” እያሉ መዓርጉን ለመቀዳጀት በየዕለቱ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ እግር ላይ ዕጥፍ ዘርጋ ይላሉ፡፡ በውትወታ ከሚያስጨንቋቸው ብፁዓን አባቶች መካከል፣ የውጭ ጉዳይ መምሪያው የበላይ ሓላፊና የአስመራጭ ኮሚቴው አባል አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ አንዱ ሲኾኑ፤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጠቋሚነት ስማቸው ከተገምጋሚዎቹ ቆሞሳትና መነኰሳት ዝርዝር እንደተያዘ ተገልጧል፡፡
ለሢመቱ እንደሚታጩም ከወዲኹ ማረጋገጫ የሰጣቸው አካል ማን እንደኾነ ባይታወቅም፣ “ስሜን በከንቱ ያጠፋሉ እንጂ ፓትርያርኩ የእኔ ናቸው፤ ጵጵስናም ይሾሙኛል፤ ለዚኽም እየተዘጋጀኹ ነው፤” እያሉ ሲወሸክቱም ተደምጠዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን የኤጲስ ቆጶሳት ሥርዓተ ሢመተ ክህነት÷ ካህናቱና ሕዝቡ ስለ ደግነቱና ትሩፋቱ፤ ስለ ንጽሕናውና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ካረጋገጡና በከፍተኛ ድምፅ “ይደልዎ፤ ይደልዎ” ብለው መስክረው በአንብሮተ እድ ከተሾመ በኋላ ተቃውሞ ቢነሣ፣ ማስታረቅ እንጂ ተቀባይነት እንደማይኖረው ይደነግጋል፡፡
በመኾኑም፣ ጥቂት ለማይባሉ ሰማዕያንና አንባብያን ቢከብድም፣ በመልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ ላይ የቀረበው የኦክላንድ ምእመናን አቤቱታ በትክክለኛው ጊዜ የደረሰ ነውና አስመራጭ ኮሚቴው በጥሞና መርምሮ ተገቢውን የጋራ አቋም ቢወስድበት፣ ነገ ከሚፈጥርብን ጸጸት ያድነናል፡፡
*               *               *
የኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ ምእመናን፣ በመልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ ላይ የሰጡባቸውና ለደብሩ ሥራ አስፈጻሚ ቀርቦ የታገዱበትና በመጨረሻም የተባረሩበት ምስክርነት፡-
መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ አራጋው፥ የበርክሌይ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ናቸው፡፡ በትምህርታቸው ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን በቤተ ክርስቲያን እንዲጋቡና ቅዱስ ቁርባን እንዲፈጽሙ አድርገዋል፡፡ ብዙ ባለትዳሮች ጋብቻ ሲመሠርቱ፤ በትዳር ውስጥ ችግር ሲገጥማቸውና የትዳር ጓደኞቻቸው በሞት ሲለዩአቸው በምክርና በማጽናናት ረድተዋል፡፡
ንብረት ስለማፍራት፡-
መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ፣ በኦሃዮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አገልግሏል፡፡ ይኹን እንጂ የኦሃዮ ቤተ ክርስቲያንን በመልቀቅ፣ የስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ እንደ ኦፊሴሊያዊ ጽሕፈት ቤት የሚጠቀምበትን የኦክላንድ መድኃኔዓለም ተቀላቅሎአል፡፡ ስለ ክርስትና ትምህርት ባለው ዕውቀቱ በማገልገል የቤተ ክርስቲያኑ የቤት ግዥ እስኪፈጸም ድረስ በደንብ ተቀባይነት አግኝቶ ቆይቶአል፡፡ በቤት ግዥው፣ ቤተ ክርስቲያኑ የቤቱ ባለቤት ሲኾን ዕዳው በእርሱ ስም ነው፡፡ ዕዳውን በአጭር ጊዜ ከእርሱ ስም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እናዛውራለን፤ተብሎ ቃል ስለተገባለት የብድሩን ስምምነት በደስተኛነት ነው የፈረመው፡፡
ነገር ግን ባንኩ፣ ብድሩን ከግለሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሊያዞር ባለመቻሉ የቤተ ክርስቲያኑ ቦርድ አስቦት የነበረው መፍትሔ ሳይሳካ ቀረ፡፡ ይኹን እንጂ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ የሚለው፤ ቦርዱ ከመጀመሪያውም ብድሩ እንደማይተላለፍ እያወቁና በተለይም የቦርዱ ሰብሳቢና የእርሱ ደጋፊዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሳየት አታለው እንዳስፈረሙት ነው፡፡ ስለ ብድሩ ኹኔታ ለማስረዳት የተደረገው ሙከራ በሙሉ እጅግ አስቸጋሪ ነበር፡፡
በመጨረሻም ቦርዱ እና መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ፣ ብድሩ እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መተላለፍ እንደሚኖርበት ባለበት ኹኔታ ላይ መስማማት ሳይቻል ቀረ፡፡ እርሱ በእሑድ የቅዳሴ ሰዓትና በተለያዩ ጊዜአት፣ ቦርዱና ቤተ ክርስቲያኑ እንዴት የማጭበርበር ሥራ እንደፈጸሙበት መናገር ቀጠለ፡፡ በእነዚኽና በሌሎች ችግሮች የተነሣ ከመድኃኔዓለም ጋር ያለው የሠራተኝነት ቅጥር እንዲሰረዝ ተደረገ፡፡ ከዚያም ቤተ ክርስቲያኑንና የቦርዱን ሰብሳቢ፤ ሌሎቹንም እንደከሠሠና ከክሡም ጠቀም ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ በጉጉት ይጠባበቅ ነበር፡፡
አዲስ ቤተ ክርስቲያን፡-
በሕጋዊ መንገድ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት የፓትርያርኩ ወይም የአካባቢው ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ይኹን እንጂ ይህን ፈቃድ አገኛለኹ በሚል ተስፋ፣ ደብረ ሰላም ኢየሱስ የተባለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን(Debre Selam Yesus Ethiopian Orthodox Church) መሠረተ፡፡ ብዙ የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ደብሩን በመተው እርሱ የመሠረተውን የደብረ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተቀላቀሉ፡፡ የማኅበረሰብ መሪዎችና አንዳንድ ባለሞያዎች ጭምር በንብረት ግዥው በደል የተፈጸመበት መኾኑን ስለአመኑ አዲሱን ቤተ ክርስቲያን በማቋቋም ከጎኑ ኾነው እረዱት፡፡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አሰባሰቡ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ብዙ መቶ ሺሕ ብር እስከማበደር ደረሱ፡፡(http://www.youtube.com/watch?v=XzgyiGmjxVc (Preview)).
የወሲብ ቅሌት፡-
መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ፣ በኦሃዮ ቤተ ክርስቲያን በሚያገለግል ጊዜ ከአንዲት ወጣት ሴት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽሞ እንደነበር ያልተረጋገጡ ወሬዎች ይናፈሱ ነበር፡፡ ዳግመኛም፣ በመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እያለ፣ እኅተ ማርያም ከተባለች ሴት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንደነበረው፣ አዲስ ወሬ ሲነገር ቆይቶአል፡፡ ነገር ግን የትኛውም ቢኾን በማንም ዘንድ ከወሬ በስተቀር ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ከዛም የአጭር ጊዜ ዕረፍት፣ በናፓ ካሊፎርኒያ በሚገኝ የመዝናኛ ቦታ በቆየበት ጊዜ የሆቴሉ ሠራተኛ የኾነችን አንዲት ሴት በተደጋጋሚ ለግብረ ሥጋ ግንኙነት የጠየቀ ሲኾን፤ ሴትዮዋ ጥያቄውን አላስተናግድም ስትለው በወሲብ ሥራ ላይ የተሰማሩ የአካባቢው ሴቶችን(call girls) ታውቅ እንደኾነ ጠይቆአል፡፡
አይቻለኹ ካለ ሰው እንደተረጋገጠው፤ በአዲሱ ቤተ ክርስቲያን ከሚያውቃቸው ኹለት ባለትዳር ሴቶች ጋር ያልተገባ ግንኙነት እንዳለውታውቆአል፡፡
ወደ ኢየሩሳሌም ባደረገው የዕረፍትና የሃይማኖት ጉዞ አብራው የተጓዘች የሴት ጓደኛ ያለው ሲኾን፤ በቆይታው ጊዜ ኹሉ አብራው በአንድ ሆቴል ክፍል ነበረች፡፡
ከአንድ ያገባች ሴት ጋር በቤተ ክርስቲያኑ አንድ ቢሮ ውስጥ ወሲብ ሲፈጽም፤ እንዲኹም፣ ከቆየች የሴት ጓደኛው ጋር በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ካለ መኝታ ቤቱና ቀደም ሲል ከአንድ ቄስ ጋር አብረው ሲኖሩ በነበረው የቀድሞ መኖርያ ሶፋ ላይ ከአንዲት ወጣት ሴት ጋር ወሲብ ፈጽሞአል፡፡
Aba Kale Tsidek going out from Continental Lodge2
ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ከአንድ ባለትዳር ሴት ጋር አንድ ሌሊት ኦክላንድ በሚገኝ ሆቴል ማሳለፉን በፎቶግራፍና በቪዲዮ ተቀርፆአል፡፡ አንድ የፖሊስ ሓላፊና የቤተ ክርስቲያኑ አንድ አባል የኾነ ሰው የሆቴሉን መቆጣጠርያ ቪዲዮ(surveillance video) በመመልከት በሆቴሉ ከተባለችው ሴት ጋር ማደሩ ትክክል መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡
ጉዳዩ እንደታወቀ፣ በመጀመሪያ የካደና በጣም የተበሳጨ ሲኾን፤ ከአባላቱ በጉዳዩ ላይ የተከራከሩትን ኹሉ ከአባልነት ሰርዞአል፡፡ ይኹን እንጂ በመጨረሻ በማስረጃ ሲረጋገጥበት ከቤተ ክርስቲያኑ ለመልቀቅ ተስማምቶአል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ የሥራ አስፈጻሚ አካልም፣ በመጀመሪያ በማገድ በመጨረሻም ከሥራው አባሮታል፡፡
ምንም እንኳን ብዙ የዓይን ምስክሮች፣ ሞቴል ውስጥ ያዩአቸው መኾኑ የተረጋገጠና ተጨማሪ የጽሑፍ ማስረጃዎች በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ካለው መኖርያ ቤት ውስጥ ቢገኝም፤ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ የቀረበበትን ክሥ ክዷል፡፡
በቅርቡም የደብረ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የሥራ አመራር ሓላፊዎችን፣ ስለ ጉዳዩ ለቤተ ክርስቲያኑ ጠቅላላ አባላት እንዳስረዳ ይፈቀድልኝ፤ሲል ጠይቆአል፡፡ ይኹን እንጂ ኹሉም ማስረጃዎች (documentary evidences) ጉዳዩን እንደፈጸመ እያሳዩ ምን ሊል እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ምንም እንኳ ከሥራ አመራር ሓላፊዎች ከጥቂቶቹ ጋር የቀረበ ግንኙነት ያለው ቢኾንም፤ ጥያቄው ተቀባይነት ያግኝ አያግኝ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም፡፡
በመጨረሻም በቤተ ክርስቲያኑ የሒሳብ ሓላፊና የሥራ አመራር አባል፣ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ 10ሺሕ ዶላር ካለደረሰኝ የተሰበሰበ ርዳታ(donation) እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋለ እንዳልታወቀ፣ በቤተ ክርስቲያኑ ጠቅላላ አባላት ስብስባ ላይ አስታውቋል፡፡ በአኹኑ ጊዜ ጉዳዩ በቤተ ክርስቲያኑ የውስጥ ኦዲተሮች እየተጣራ ነው፡፡
ምድረ አሜሪካን በረገጡበት የመጻተኝነት(የእንግድነት) ወራቸው፣ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅን አምነው የተጠጉትና በቃለ ጽድቅ ሴሰኝነት ባለቤታቸውን ተነጥቀው ትዳራቸው የፈረሰባቸው አባወራ አቤቱታ
ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
ለስደተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ኦክላንድ፣ ካሊፎርንያ
አመልካች፡- የሻምበል ከፍያለው
አድራሻ፡- በአሜሪካ ሳንዲያጎ እና ኦክላንድ ካሊፎርንያ
ጉዳዩ፡- በኦክላንድ ደብረ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳደር ካህን/መነኵሴ በመልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ አርጋው የተፈጸመውን የሥነ ምግባር ጉድለት ይመለከታል
እኔ አመልካች፥ በትውልዴ ኢትዮጵያዊ፣ በእምነቴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ የኾንኩ እኖርበት ከነበረው ባሕር ዳር ከተማ በዲቪ ሎተሪ ዕድል ምክንያት፣ ከሕግ ባለቤቴ ከወ/ሮ ብዙአየኹ ገረመው ጋር በየካቲት ወር 2012 ወደ አሜሪካን አገር አብረን መጣን፡፡
እንደመጣን፣ በሳንሆዜ ከተማ ዐርፈን ሳለ በአገር ቤት በነበርኩበት የሥራ ሞያዬ፣ የዕንጨት ቀራፂ ሞያተኛ በመኾኔ የኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ፣ መንበረ ታቦት በዕንጨት ቀራፂነት እንድሠራ በ3ሺሕ500/ሦስት ሺሕ አምስት መቶ/ ዶላር ተዋውለንመንበረ ታቦቱን ለመሥራት ወደ ኦክላንድ መጣኹ፡፡ ባለቤቴ ወ/ሮ ብዙአየኹ ግን እዚያው ሳንሆዜ እንድትቆይ ተስማምተን አገልግሎቴን ቀጠልኩ፡፡ ይህ በእዚኽ እንዳለ አባ ቃለ ጽድቅ ባለቤቴን በማግባባት ወደ ኦክላንድ እንድትመጣ ገፋፍተው እንድትመጣ ኾነ፡፡ ለጊዜውምመጠጊያ ያጣን ምእመናን እና ስደተኞች ስለነበርን፣ አባ ቃለ ጽድቅ ያሉንን በሙሉ በእምነት እየተቀበልን ያለአንዳች ጥያቄም ኾነ ጥርጣሬ እሳቸው ያሉንን እናደርግ ነበር፡፡ የደብረ ሰላም ኢየሱስ ምእመን የሚሰጡንን ቁሳቁሶችና ርዳታም እየተቀበልን የመንበረ ታቦቱን ሥራ ለማጠናቀቅ በቃኹ፡፡
በሥራውም ላይ በነበርኩበት ሰዓት ከአባ ቃለ ጽድቅ የተዋዋልኩት 3500.00 ዶላር ቢኾንም፤ በእጄ የተሰጠኝ የገንዘብ መጠን 500.00/አምስት መቶ/ ዶላር ብቻ ነበር፡፡ ቀሪውን ሒሳብ ከቀን ወደ ቀን ይሰጡኛል እያልኩ ስጠባበቅ እንደ አጋጣሚ ኾኖ ሳንዲያጎ በተመሳሳይ ሥራ እንዳገለግል ሥራ አግኝቼ ወደ ሳንዲያጎ ሔድኩ፡፡
ወደ ሳንድያጎ በምሔድበትም ሰዓት፣ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ በመኪና የሸኙኝ፣ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ እና ባለቤቴ ነበሩ፡፡ አውሮፕላን ማረፊያ በደረስኩበትም ሰዓት መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ እኔን በማቻኮል ከመኪና እንድወርድ እየጠየቁ እያለ በተጨማሪም ባዶ ሉክ ወረቀት አምጥተው፣ “ከወደታች በኩል ስምህን ጽፈህ ፈርም” ብለው ትእዛዝ ሰጡኝ፡፡ እኔም በአንድ በኩል እያጣደፉኝ ስለነበር፣ ይህን ባዶ ሉክ ወረቀት ለምን ሥራ ላይ ለማዋል እንደፈለጉ ጊዜ አግኝቼ ለመጠየቅ አልቻልኩም ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይም አባ ቃለ ጽድቅን በአባትነታቸው ስለማከብራቸው፣ ምንም ዓይነት ጥያቄ ሳላቀርብ ስሜን በመጻፍ ፊርማዬን በባዶ ሉክ ወረቀት ላይ አስፍሬ መለስኩላቸው፡፡
ሳንድያጎ ከሔድኩ በኋላ በየጊዜው ከባለቤቴ ጋር በስልክ እንገናኝ ነበር፡፡ ከትንሽ ቀናት በኋላ ግን ምሽቱን በሙሉ ከመልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ጋር አብረው በመኾን እንደምታሳልፍ ለመረዳት ቻልኩ፡፡ ይህንንም ከተለያዩ ምንጮች ከሰማኹ በኋላ ታሪኩን ለማጣራት ወደ ኦክላንድ መጣኹ፡፡ከመጣኹም በኋላ የሕግ ባለቤቴ እንደወትሮዋ ለእኔ ያላት አስተያየትም ኾነ ቀረቤታ በጣም ተለውጦ አገኘኹት፡፡ ለምንስ ከመነኵሴ ቤት ከመቅደስ ጀርባ ገብተሽ ታመሻለሽ? ደግሞስ፣ በግል ክፍላቸው ውስጥ ጊዜ ታጠፊአለሽ? ብዬ ብጠይቃት፣ አንዳንድ የማደርጋቸው ርዳታዎች ስላሉ ማድረግ አለብኝ፤ በማለት መልስ ሰጥታኝ ከልቤ አዝኜ፣ ጉዳዩን ለፈጣሪ ሰጥቼ ወደ ሳንዲያጎ ተመለስኩ፡፡
ይህንንም ያልጠበኩት በቤተ ክርስቲያን ጠለላ ሥር እንደዚኽ ዓይነት ድርጊት ሲፈጸም፤ አቤት ለማለትም በጊዜውና በሰዓቱ ከጥርጣሬ በስተቀር ምንም ማስረጃ ስላልነበረኝ ጉዳዩን ለፈጣሪ ከመስጠት በስተቀር ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር፡፡ በሰዓቱና በወቅቱ ግን ጥርጣሬዬን ለባለቤቴ ገልጩላት የገንዘብ ርዳታም ኾነ ድጋፍ እንዳቆምኩ ለሕግ ባለቤቴ ገልጩላት ነበር፡፡
ይህም ሒደቱ በዚኽ ጉዳይ ላይ እንዳለ አንድ ምሽት፤ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ አርጋው የእኔን የሕግ ባለቤት ይዘው በኦክላንድ መኝታ ክፍል ሆቴል ቤት፣ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት አብረው ገብተው የሕግ ባለቤቴን በመድፈር የቆሞስነት የቤተ ክህነት ማዕርግ ያላቸው ድንግላዊ መነኵሴ ባለቤቴን ይዘው በሆቴል መኝታ ክፍል አደሩ፡፡ በነጋታው 1:00 ሰዓት ጠዋት ላይ ወጡ፡፡
መነኵሴው በአንዳንድ በዚኹ ሥነ ምግባር ብልሹነት ይጠረጠሩ ስለነበር ያንን ክትትል በማድረግ ላይ የነበሩ መእመናን፣ ፎቶ እና ቪድዮ በማንሣት የእኔን የሕግ ባለቤቴንና የመነኵሴውን የሥነ ምግባር ብልሽት አብረው ካደሩበት መኝታ ክፍል ሲወጡ በቪዲዮ እና በፎቶ ቀርፀውት ይገኛል፡፡
ይህንንም ፎቶ እና ቪዲዮ ያነሡት ምእመናን፣ ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ ካቀረቡ በኋላ ለጊዜው ካህኑን ከሥራ መደባቸው አግደዋቸዋል፡፡ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ፥ ጉዳዩ፣ የክህነትን ጥያቄ የሚመለከት ስለኾነ ለበላይ ክፍል ማለትም ለቤተ ክህነቱ በተለይም ለቅዱስነታቸው ውሳኔ እንዲሰጡበት አስተላለፈናል፤ በማለት በጉባኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ኾኖም የእኚኽ መነኵሴ የሥነ ምግባር ብልሽት ከቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊ ሥነ ሥርዓት/አመራር/ የወጡ፤ ምንኵስናዊ ማዕርጋቸውን ያዋረዱና ያረከሱ መኾናቸው ይህ ድርጊታቸው ስለሚያሳይ፣ ስደተኛው ሲኖዶስ ይህን የሥነ ምግባር ብልሹነት ተከታትሎ አንድ ዓይነት ውሳኔ እና ርምጃ እንዲያስተላለፍ በትሕትና እጠይቃለኹ፡፡
የእኚኽ ሰው በሴቶች ላይ ያላቸው የሥጋዊ ጥቅም ፍላጎት፣ ሴቶችን እንደማንኛውም ግልገሎቻቸውና ጠቦቶቻቸው መጠበቅና መንከባከብ ሲገባቸው፣ ሴት ልጅን ግላዊ ለኾነ ሥጋዊ ጥቅም ብቻ እንደሚገለገሉባት ያሳያል፡፡ የእኚኽ መነኵሴ ድርጊት አኹን በማስረጃ ስለተያዘ እና ስለቀረበ፣ የስደተኛው ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ተልኳል የተባለውን የፎቶ እና የቪዲዮ ማስረጃ ተቀብሎ አስፈላጊውን ሙሉ ምርመራ ካስፈለገም እኔን በቃል በማነጋገር እና የምስክርነት ቃል በመውሰድ የኢትዮጵያዊት ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት ሥነ ሥርዓትም ኾነ ፍትሕ ነገሥቱ በሚያዘው መሠረት አስፈላጊውንና ተገቢውን ርምጃ መውሰድ አለበት፤ የሚለውን አስተያየቴን ከታላቅ አክብሮት ጋር አበረክታለኹ፡፡
እኔ፣ አቶ የሻምበል ከፍያለው ያቀረብኩትን አቤቱታ የስደተኛው ሲኖዶስ የደረሰውን የሥነ ምግባር ብልሹነት አስፈላጊውን ርምጃ ወስዶ፣ የወሰደውን ርምጃና ውጤቱን እንዲያሳውቀኝ ስል በአክብሮትና በትሕትና አመለክታለኹ፡፡
አመልካች
የማይነበብ ፊርማ አለው
ሻምበል ከፍያለውthe scandalous Aba Kale TsidekAba Kale tsidek scandal02Aba Kale tsidek scandal03

No comments:

Post a Comment

wanted officials