Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 12, 2016

አቶ አብርሀ ደስታ ከእስር ተፈታ

 ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ  በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ሲንገላታ የነበረው የአረና ትግራይ ፓርቲ አባል መምህር አብረሃ ደስታ ከእስር ተፈቷል።
አቶ አብርሃ ደስታ ነሀሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ የተባለ ቢሆንም፣  ችሎት ተዳፍረሃል ተብሎ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር እንዲቆይ ተደርጓል። አብርሃ ደስታ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚፈጽማቸውን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ሲያጋልጥ ቆይቷል።

 


1
Audio Player
የአረና ትግራይ ፓርቲ የሥራ አመራር አባል የነበረው አቶ አብርሀ ደስታ ዛሬ ከእስር መፈታቱ ታወቀ። አቶ አብርሀ ከእስር መፈታት የነበረበት ከወራት በፊት ቢሆንም ፍርድ ቤት ተጋፍተሃል በሚል ምክንያት ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ተጥሎበት ቆይቷል።
የአረና ትግራይ የሉአላዊነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ የስራ አመራር አባል የነበረው አቶ አብርሀ ደስታ ለሁለት አመት በእስር ከቆየ በኃላ ዛሬ አመሻሹ ላይ መፈታቱ ታወቀ።“ይሄ ነው የሚባል መጉላላት ዛሬ ባይደርስብኝም ከግቢው ለመውጣት ከምጠብቀው በላይ ጊዜው ረዝሞብኛል” በማለት አቶ አብርሀ የእስር ፍቺ ሂደቱን ለመግለፅ ሞክሯል። የፌደራሉ አቃቤ ህግ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም በነዘላለም የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው አስር ሰዎች መካከል አንዱ አቶ አብርሀ ደስታ ነበር።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
13645270_171306613284425_8909679246733704466_nabrha1

No comments:

Post a Comment

wanted officials