Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 24, 2016

አሳሳና አዳባ በህዝብ ተቃውሞ እየተናጡ ነው – ተቃዋሚዎች የአላሙዲ አጥሮችን ለመንገድ መዝጊያ እየተጠቀሙበት ነው


adaba adabs asasa 2 asasa asasa.jpg2
 ምዕራብ አርሲ አሳሳና አዶላ በህዝብ ተቃውሞ ውጥረት ውስጥ እንዳሉና አካባቢውም በአጋዚ ሰራዊት ቢወረረርም ሕዝቡ የተለለያዩ ነገሮችን በየአደባባዩ በማንደድ በአጋዚዎች ላይ መንገድ በመዝጋት ላይ እንደሚገኝ የሚደርሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::
እንደ መረጃዎች ከሆነ በም ዕራብ አርሲ አሳሳ ከተማ ከሕዝብ ተቀምቶ ለአላሙዲ የተሰጠው መሬት የታጠረበትን አጥር ሕዝብ ነቃቅሎ መንገድ እየዘጋበትና እያቃጠለበት እንደሚገኝ የዜና ምንጮች አስታወቀዋል::
በተመሳሳይም በአዳባ ከተማ እንዲሁም የመንግስት እርሻዎች የታጠሩበት አጥሮች እየተገነጣጠሉ አጋዚ ወደ ከተማው እንዳይገባ በ እሳት እየተቀጣጠለና ለመንገድ መዝጊያነት እንዲውል መደረጉ ታውቋል:: በድንጋይ እና በሚቀጣጠል እሳት መንገዶች በመዘጋጋታቸው በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የመኪና እንቅስቃሴ በአካባቢው እንደሌለ ተረጋግጧል::
ምዕራብ አርሲ በዶዶላ; በአሳሳና በአዳባ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው:: ህዝቡም ጮክ ብሎ ተቃውሞውን በመንግስት ላይ በመግለጽ ላይ ይገኛል::



No comments:

Post a Comment

wanted officials