Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 21, 2016

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በኢንተርፖል ተይዞ ወደ አዲስ አበባ መጣ

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው በክሪ ሙሀመድ ሹሬ በኢንተርፖል አማካኝነት ዛሬ ጠዋት ከኩዌት ተይዞ መጥቷል።
ግለሰቡ ከ5 ዓመት በፊት ሙሀመድ አብዱልአዚዝ በሚል ሀሰተኛ ስም ኤጀንሲ እንዳለው በማስመሰል በማታለል በሕገወጥ መንገድ አንዲት ወጣትን ወደ ኩዌት ልኮ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ገልጿል።
ተጠርጣሪው ወደ ኩዌት በሕገወጥ መንገድ የሄደችው ወጣት ከፋተኛ ስቃይ ደርሶባት ህይወቷ አልፎ አስከሬኗ ወደ ሀገር ቤት መጥቶ ሥርዓተ ቀብሯ እንደተፈፀመም ኮሚሽኑ አስታውሷል።
በዚህ ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ተጠጣሪ በክሪ መሀመድ ስሙ በኢንተርፖል አባል ሀገራት መበተኑን ተከትሎ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና በፌዴራል ፖሊስ ኢንተርፖል አማካኝነት ዛሬ ጠዋት ከኩዌት ተይዞ መምጣቱን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ድንበር ዘለል ተፈላጊዎች ክትትል ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሻምበል አሰፋ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የምርመራ ሥራውን እንደሚቀጥል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ማስታወቁን ኢብኮ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials