Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 4, 2016

ክብረ ቢሶችን የሚያከብር ሃገር ( ሄኖክ የሺጥላ )



ክብረ ቢሶችን የሚያከብር ሃገር ( ሄኖክ የሺጥላ )
ታሪክ እንደሚዘግበው ፥ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1478 የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ላንድ ለታወቀ ሰው የክቡር ሹመት መስጠት ፈልጓል። ይህ ሰው የቅዱስ ጳውሎስ ቤ/ክርስቲያን አገልጋይ ብቻም ሳይሆን የንጉስ ኤድዋርድ አራተኛ ሚስት ወንድምም ነው።
ታላቅ ሰው ። ባለ ክብር ፥ ባለ ሃብት ፥ በስራው የጀገነ ስለሆነ የኦክስፎርድ ዝምድናውን ለማጠናከር ዘዴ ዘይዷል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ለዚህ ሰው የክብር ሽልማት ይሸልመዋል ( ይህ ሽልማት በዘመናዊ የእውቀት ወቄት ሲለካ የክብር ዶክትሬት ከሚባለው ጋ አቻ የሆነ ነበር ) ። ይህ ሰው ስሙ ውድቪል ይባላል ። ውድቪል በታሪክ የመጀመሪያው ባለ ክብር ዶክትሬት እንግሊዛዊ መሆኑ ነው ። ብዙም ሳይቆይ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የቻንስለርነት ስልጣን ተሰጠው። የዚህን ሰውዬ ክብረት ተከትሎ በእንግሊዝ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ( በ 16ኛው እና 17ኛው ክፍለ ዘመን ) ፥ ይህ ሰው እየመረጡ መሾም እንደ ባህል ብቻ ሳይሆን እንደ እስትራቴጂም ጭምር ተያዘ። « Throughout the 16th and 17th centuries, prestigious institutions like Oxford would don hundreds of other men, all of whom were members of the noble elite, similar degrees. In 1642 alone, some 350 doctorates were doled out by Charles I — many of which went directly to members of his court.»
በዚህ ከማብረቅረቅ ባለፈ ምንም ፋይዳ በሌለው ዲግሪ የሚንቆጠቆጡ ( ornamental) ባለ ክብር ዶክተሮች በአማሪካም እውቅና ይሰጣቸው ጀመር ።
እነ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ( ክብሩ ቢገገባቸውም ) ሽልማቱን ያገኙበት መንገድ የሸላሚዎችን ወዳጅ ፍለጋ እንጂ የነፍራንክሊንን እፅብ ስራ መሰረት አድርጎ የሆነ እንዳልነበረ ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ ። ይህ የክብር ዶክትሬት እንደ አሸን በፈላበት ዘመን ታዋቂው አማሪካዊ ቻርልስ ፎሰተር ስሚዝ ከይህ በታች ያለውን ተናግሮ ነበር
« “The mode in which honorary degrees are conferred in this country is a sham and a shame. It is so easy to get a degree — so many men of slight acquisitions have obtained a degree -- that it is now the way to apply for these honors. If the secret sessions of college corporations were made public, there would be an astonishing revelation of intimations and open requests and endorsements. Members of the faculties of colleges are constantly applied to lend their influence to secure a doctorate for this person or that.”
ከእነዚህ በክብር ዶክትሬት ያጌጡ ተሸላሚዎች ፥ አብዛኛዎቹ የክብሩ የምር እንዲሆንላቸው የሸለማቸውን የትምህርት ተቋም በጥቅማጥቅም እያስገደዱ የማጭበርበር ስራም ለመስራት ጥረት ያደርጉ እንደነበር ታሪክ ይዘክራል ።
በሃገራችን ኢትዮጵያም መጀመሪያ በስራቸው የላቁ እና የረቀቁትን በመሸለም የተጀመረው ይህ የክብር ዶክትሬት ( ከነዚህ ውስጥ ይገባቸው ነበር ብዬ የማስበው እንደ ነ ጥላሁን ገሰሰ ፥ ዶ/ር ከበደ ሚካኤል እና ወዘተ መሃል ፥ እንክርዳዶቹ እና በምን አይነት መስፈርት የክብር ዶ/ክትሬት እንደተሰጣቸው የማናውቀው ሌሎች ተፈጠሩ ። ሁኔታው በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በ ከ 15ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ የነበረውን የእከክልኝ ልከክልህ ፥ በዝምድና የተጠነፈገ የመሿሿም ባህል ሲሆን የምናየው ፥ ከእንግሊዝ የሚለየው ግን ባለንበት ክፍለ ዘመን ፥ ከሰውነት በታች ወርደው ፥ ሃገር አዋርደው ፥ ህዝብ አዋርደው ፥ በህዝብ የተከሀብሩ መሪዎች ተብለው መሸለማቸው ብቻ ነው ። በእንግሊዝ ቢያንስ ከተሸላሚው ትከሻ ሰፊነት ጀርባ ህዝብን የሚያስቆጣ ገድልም ይሁን ድል የተሸከመ ባለ ከል ታሪክ ሰው አይሸለምም ነበር ።
እኛ ግን ያዋረዱንን ፥ ልጆቻንን ገለው ከል ያለበሱንን ፥ በዝሙት እና በሴስ ፥ በሱስ እና በ ክብረ ነካዊ ማንነታቸው ሃገር ያወቃቸው ፥ ፀሃይ የሞቃቸው « አለሌ ሽማግሌዎች» በክብር ሲሸለሙ ሳይ ፥ እውነትም ይህ ህዝብ ቅኔ ነው እንድል ሆኛለሁ ። ያከበሩን ተዋርደው ፥ ያወረዱን የከበሩበት እና የሚከበሩበት ሃገር ልጆች መሆናችንን ሳስብ ሬት ሬት የሚል ነገር ይሰማኛል ። ምሬት እና ብሶት እንደ ናይል ከጫፍ ጫፍ ሽንጡን ዘርግቶ ፥ በዋይታ ፈረሰኛ ቀየውን ፥ መንደሩን ገለባብጦ ፥ የሶስት ወር ልጅ ላይ ቤት ላፈረሰ ስርዐት የክብር ዶክትሬት የሚሸሉም ተቋማት ምን አይነት ትውልድ ቀርፀው ሊያወጡ እንደሚችሉ ሳስብ ፥ ካለማሰብ በሚመጣው ሰላም እረፍት ለማግኘት
ሁሉን ችላ ብለው ፥ ደድበው እና ደንዝዘው በሚኖሩት ሰዎች መቅናት እስክመኝ ድረስ በመረዳቴ እቆጫለሁ ። ይህ ህዝብ « ክብረ ቢሶችን ለማክበር ስንት አመት ፈጀበት ግን ?»

No comments:

Post a Comment

wanted officials