Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 4, 2016

ሐብታሙ አያሌው የህዝብ ልጅ መሆኑን ለማሳየት ነገ ማለዳ ፍርድ ቤት እንገኝ



ሐብታሙ አያሌው የህዝብ ልጅ መሆኑን ለማሳየት ነገ ማለዳ ፍርድ ቤት እንገኝ
================
ለአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ታስሮ በነጻ ፍርድ ቤት ያሰናበተው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው አቃቤ ህግ ይግባኝ የጠየቀበት በመሆኑ ነገ 6ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል፡፡
ሐብታሙ በይግባኙ ምክንያት ከአገር ወጥቶ እንዳይታከም በመደረጉም እስካሁን ድረስ በማስታገሻ መድሃኒት እየተሰቃየ ይገኛል፡፡የነገው ውሳኔ በሐብታሙ ህይወት ላይ የሚኖረውን አስተዋእጾ ግምት ውስጥ በመክተትና ሐብታሙና ጓደኞቹ የተሰቃዩትና ያለአግባብ የታሰሩት የህዝብ ልጆች መሆናቸውን ለማሳየት ሁላችንም በቦታው እንገኝ፡፡ይህንን መልእክት ሁሉም ጋር እንዲደርስ ሼር ያድርጉ
የችሎቱ ቦታ -6 ኪሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰዓት --- ጠዋት 3፡00 ሰዓት

No comments:

Post a Comment

wanted officials