Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 26, 2016

በጎንደር ወጣቶችና በሕወሓት ወታደሮች መካከል ግጭት ተነሳ









በጎንደር እሁድ ሰልፍ ይኖራል ብአዴን ሰልፉን ለማስተጓጎል አድማ በታኝ ፖሊስ መድቧል
በጎንደር ከተማ ከትላንትና ምሽት ጀምሮ ሕወሓት ያሰማራቸውና ጨለማን ተገን ኣድርገው ወጣቶችን ሊያፍኑ ሲሞክሩ የነበሩ የደህንነት ሃይሎች የኣፈና ድርጊታቸውን ዛሬም በቀን በቀጠሉበት ሰኣት ላይ በተፈጠረ ኣለመግባባት በጎንደር ወጣቶችና በሕወሓት ወታደሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የተኩስ ድምጾች መሰማታቸውን በኣከባቢው የሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል።
የእሁዱን ሰልፍ ያስተባብራሉ ለኮሎኔል ደመቀ የፍርድ ቤት ቀጠሩ በፍርድ ቤት የሚገኙ ደጋፊዎችን እያስተባበሩ ይሰበስባሉ የተባሉ ወጣቶችን ለማፈስ የተሰማራውን ሃይል የጎንደር ወጣቶች እንዳስደነበሩት ቀበሌ 18 ኣከባቢ የሚገኙ ሁኔታውን የሚከታተሉ ወገኖች ተናግረዋል። ወያኔ የፊታን እሁድ ይደረጋል የተባለው ሰልፍ እንዳስፈራውና እንዲራዘም በውስጥ እየተማጸነ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
በጎንደር እሁድ ሰልፍ ይኖራል
ብአዴን ሰልፉን ለማስተጓጎል አድማ በታኝ ፖሊስ መድቧል
እሁድ ሀምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ በብአዴን አመራሮችና በሕዝብ ሽማግሌዎች መካከል እስካሁን ስምምነት አልተደረሰም። ገዥው ቡድን ችማግሌዎችን ለየብቻ እየወሰደ በማስፈራራት እና በማባበል ሰልፉን እንዲሰርዙ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። ሆኖም ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በነበረው ስብሰባ ሰልፉ እንደማይቀር ከሕዝብ የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንቅጩን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎ ለኣማራ ክልል አድማ በታኝ ፖሊስ ወደ ሰልፉ የሚወጡ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ብሎም ወደ መስቀል አደባባይ መሔጃ መንገዶች እንዲዘጉ እንዲያደርግ ከብአዴን ጽ/ቤት ደብዳቤ መላኩን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ልዩ ኃይል ፓሊሶችም ልዩ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል።
ይህን ተከትሎ በሰልፉ ለሚሳተፉ አንዳንድ ግለሰቦች “ሰልፉ ቦታ ትሄዳላችሁ?” ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ “መትረየስ ቢጠመድም አንቀር!” ሲሉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials