Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 19, 2016

አትሌት ስንታየው መርጋ እጅጉ የአበረታች መድሃኒት መጠቀሙን ይፋ አደረገ


ዛሬም ብዙ ሰንታየዎች አሉ!sintayehu merga

በዚህም ማህበሩ ለኢትዬጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ስለ ጉዳዪ አሳውቋል።
ቶማስ አበበ | ለዘ-ሐበሻ
አትሌት ስንታየው መርጋ ማን ነው?
አትሌት ሰንታየው የፖሊስ ራጭ ነው።ውድድር የጀመረው ቆየት ቢልም ትልቁ ውጤቱ ግን በ2015 ነው ያሰመዘገበው።ሰንታየው የ2015 የሆንግ ኮንግ ማራቶን አሸናፊ ነበር።በእስያ እንደ ትልቅ የማራቶን ውድድሮች የሚቆጠረውን የሆንግ ኮንግ ማራቶን ያሸነፈው ይህ አትሌት 2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ በመግባት ነው።በውድድሩም አሸናፊ ሰለሆን በወቅቱ 65 ሺ ዶላር ተሸልሟል።በዙህም ውድድር በ2012 በሀገሩ ልጅ ደረጄ አበራ የተያዘውን የቦታው ክብረ ወሰን ለመስበር ተቃርቦ ነበር።በ2013 የአሰር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን በ29 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ ያጠናቀወበት ጥሩ ሰዓቱ ነበር።
አትሌቱ ምን ይደርስበት ይሆን?
አትሌት ስንታየው አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጣለበትን የአራት አመት እገዳ እሰኪያጠናቅቅ ከሩጫ ውጪ ይሆናል።ከዚያን በሃላ ይመለሳል።እዚህ ጋር አትሌቱ ቢመለስ የቆሸሸ የሀገር ስም ግን አይመለስም።
የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ማህበር በአሁኑ ሰዓት ሰድስት ኢትዮጵያዊ አትሌቶችን ላይ ምርመራ እያደረገ ነው።ኢትዮጵያ ከሩሲያ ፣ዮክሬን እና ሞሮኮ ቀጥላ ልክ እንደ ኬንያ በሰፊው ትጠረጠራለች።እንደ ሰንታየው የመሰሉ አትሌቶች ደግሞ ነገሩን ከጥርጣሬ ወደ እውነታ ይቀይራሉ።
አሁን ያልተደረሰባው ብዙ አትሌቶች መዳኒት እየወሰዱ እየሮጡ እንደ ሆነ ወደ መሮጫ ስፍራዎች ሲሄዱ እንደ ቀልድ ይሰማሉ።
በአበረታች ንጥረ ነገር ማሰመጣት እና ለአትሌት መስጠት ላይ ከመጋረጃ በስተ ጀርባ ያሉት እንማን ናቸው?
1/የቀድሞ የተወሰኑ አትሌቶች
እዚህ ላይ በርከት ያሉ ጀግኖች አትሌቶቻችን የሉበትም ።አንዳንድ ለሆድ አዳሪ ግን መድሃኒቶች ያስመጣል ይሸጣል።የወሰዱ አትሌቶችም ከነዚህ አትሌቶች ምክር ይሰጣቸዋል።
2/የአትሌት ማናጀሮች
ኢትዮጵያ ውስጥ የአትሌት ማናጀር የሆኑት በአትሌት ሰም ተራውን ዜጋ ወደ ውጪ ለመላክ እና ሀብት ለመሰብሰብ እንደሆን እውነታ ነው።ብዙዎች የአትሌት ታሴራ እየሰጡ ለተራው ዜጋ አትሌት ነው ብለው ከ400 መቶ ሺ ብር እየተቀበሉ ነው።ባለፍት አመታት ደግሞ አበረታች መዳኒት መቸብቸብ ጀምረዋል።
3/የተወሰኑ የፌደሬሽኑ ሰራተኖች
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በዘር የተሳሰረ እና የተደራጀ በመሆኑ ህገወጥነት በቀላሉ ተንሰራፍቶበታል።በአንድ ወቅት አንድ አትሌት ቃለ መጠይቅ ሳደርግለት የነገረኝ እዚህ ጋር ላስታውሰ።
«ወደ እዚህ ቢሮ መተህ በኦሮምኛ እና በትግረኛ ከዳይሬክተሩ ጋር ካወራህ የፈለክበት ሀገር ሄደ ትወዳደራለህ ይፈቀድልሃል ፣ነገር ግን በአማርኛ ካወራክ አይፈቀድልህም ብሎኝ እንባ የተናነቀው አትሌት አስታወሰኝ»በዘር መቀመጥ ፣በጎጥ መፈራጀት ፣በፖለቲካ የፌደሬሽኑ ሃላፊ መሆን የአበረታች መዳኒት ሽያጬን ህጋው አድርጎታል።
የአበረታች መዳኒት አዋጭ ቢዝነዝ የሆነው ለምንድ ነው?
መዳኒቱ በአጭር ያከብራል።አንድ አትሌት ይህን መዳኒት በእንክብል ለመውደድ እስከ 10 ሺ ብር ሲያወጣ ፣በመርፌ ለመወጋት ከ15 እስከ 35 ሺ ብር ይከፍላል።ይህ ብር ነው ግለሰቦችን በዘር አዋዶ ንግድ ሲሆን ሀገር ግን ጥላሸት ለበሰች።
ዘዋዋሪዎች የት ነው ያሉት?
ወያኔን ለመቃወም በእየ ሰፈሩ ከተንቀሳቀሰክ አሸባሪ ነህ።ጥይትም ይመዘዝብሃል።የሀገርን ስም ለማጥፋት መዳኒት በእየሰፈሩ ስታዞር ግን አይተው እንዳላዪ ይሆናሉ።
አዘዋዋሪዎቹ ሰራቸውን በስፋት የሚሰሩት አትሌቶች ልምምድ በሚሰሩበት ቦታዎች መሆኑ መንግስት አላየውም ማለቱን ትዝብት ውስት ይከተዋል።
መዳኒቱ በስፋት እንጦጦ ተራራ ላይ ፣ሰንዳፋ፣ኮተቤ፣ሰሚት እና በቆጂ እንደሚሸጥ አትሌቶች ነግረውናል።ይህን ፌደሬሸኑ ያውቃል።ታዲያ ካወቀ ለምን እርምጃ አይወስድም ልትሉኝ ትችላላቹ።እንዴት ስጋው በስጋው ይጨክናል።ተቆጣጣሪው እና ሽያጭ በስጋ ቤተሰብ ሆነው በጥቅም ተሳስረዋል።
ዝምታ ምን ያመጣ ይሆን?
ዝምታው ልክ እንደ ሩሲያ እገዳ ያመጣል።
ዝምታው የሀገር ስም ያጠፋል።
ዝምታው ፣ ዝምታው በዚህ ስዓት ውስጥ ያለውን ሌባ ነጋዴ ብቻ ይጠቅማል።
የችግሩ ፈጣሪ ማነው?
የአበረታች መዳኒት እንደ ልብ እንዲሸጥ መንገድ የከፈተው የዘር ፖለቲካ ነው።ስራው የሚሰሩት በአሰተሳሰብ ወያኔ የሆኑ ናቸው።አንዱ ላይ እርምጃ ከተወሰደ ግንዱ ይመታል።ግንዱ ደግሞ ወያኔን ያጋልጣል።ሌሎች ላይ ጡንቻው የሚያሳየው ወያኔ ለምን እነዚህ ላይ አላሳየም ብለው መጠቅ መልሱን ያሳያል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials