Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 22, 2016

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተፈረደባቸው

ኤርትራ ድንበርን በማቁዋረጥ አርበኞች ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ሲያመሩ ተይዘው የሽብር ክስ የቀረበባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ተከሳሾ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካሳይ ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስረዳቱ የጥፋተኝነት ፍርድ መስጠቱን 14ኛ ወንጀል ችሎት ገልጹዋል።
ተከሳሾች 141 መከላከያ ምስክሮችን አስመዝግበው እንደነበር አስታውሶ፣ በተከሳሾች በኩል የተመዘገበው ጭብጥ ግን የፈጸሙት ተግባር ወንጀል ነው ወይስ አይደለም በሚል እንዲመሰክሩ በመሆኑና አንድን ተግባር ወንጅል መሆን አለመሆን በህግ እንጂ በምስክር ስለማይረጋገጥ የምስክሮች መሰማት አግባብነት ስለሌለው መታለፉ ተወስቱዋል። 
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሀምሌ 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቱዋል።
ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉበት የህግ ክፍል የጸረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 7(1) ን መተላለፍ የሚል ነው።
Belay Manaye's photo.

No comments:

Post a Comment

wanted officials