Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, July 20, 2016

በያቤሎ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

በያቤሎ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ
ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ሃምሌ 13 ቀን 2008 ዓም የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት ተቃውሞ ሲያካሂድ ውሎአል።
ተቃውሞውን የጀመሩት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የከተማውም ህዝብ ተቀላቆሎአቸዋል። ከጥንት ጀምሮ የሞያሌ ወረዳ በቦረና ዞን ይተዳደር እንደነበር እየታወቀ፣ በየትኛውም ቦታ ባልታዬ ሁኔታ ወረዳው በሁለት ክልላዊ መንግስት ሲተዳደር መቆየቱ አግባብ ባለመሆኑ ወደ ቦረና ዞን እንድትመለስ የሚል ጥያቄ ቀርቧል።
ሰልፈኞቹ “ ባልተማሩ ሰዎች አንተዳደርም፣ በያቤሎ አካባቢ ዩኒቨርስቲ ይሰራልን፣ ፍትህ ይከበር፣ እውነተኛ የዳኝነት ውሳኔ ወስኑ፣ ነገሌ ወደ ቦረና ዞን ይከለልልን፣ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብታችን ይከበር፣ ይህ መንግስት መብታችንን ሊያከብር አልቻለም” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በመጨረሻ የአገር ሽማግሌዎች ከባለስልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ ከተደረገ በሁዋላ ባለስልጣናቱ፣ ጥያቄያችሁን ለመመለስ የአንድ ሳምንት ጊዜ ስጡን በማለት ህዝቡን አረጋግተው ተቃውሞው በቀጠሮ እንዲተላለፍ አድርገዋል።
ሞያሌ ከተማ ላለፉት 25 አመታት በሶማሊ እና በኦሮምያ ክልሎች በጋራ ሲተዳደር ቆይቷል። በከተማዋ ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲካሄዱ ቆይቷል። በዚህ ሳምንት በምእራብ ሃረርጌ በአሰቦት ፣ ሂርና እና ምስራቅ ሃረርጌ እንዲሁም በምእራብ ሸዋ በጀልዱ አካባቢዎች ተቃውሞች ተካሂደዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials