Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 11, 2016

“እኔም ጎንደሬ ልሁንና ሹሙኝ” – ክፍል ሁለት (ከመኳንንት ታዬ)

“እኔም ጎንደሬ ልሁንና ሹሙኝ” – ክፍል ሁለት (ከመኳንንት ታዬ)

ንዑስ  ርእስ ፤-ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ*ዶሮ አንዳለችው*
ባለፈው ሳምንት ከላይ በርእሴ ላይ ባለው ርእስ  አንዲት አጠር ያለች መጣጥፍ  ለአንባቢያን ማቅረቤን ተከትሎ አስተያቶች ቢኖሩም ሁሉም አዋቂም ፃፋቸው ጨዋ ገንቢነታቸው የእኛ እኛነት ከምን ላይ እንደ ደረሰ  አመለካከቶች  ነበሩና ያንኑ ለማጠናከር የተሻለ ሰውነት በምን አይነት የሞራል ስብና ብንገነባው የትላንትናው ማንነት ከወጣበት መስመር ወደተሻለ መሃል እንኳን ባይሆን ወደተሻለ ዳር  እናስጠጋዋለን  የሚለውን መነጋገ ሪያ ነጥብ  ከግምት በማስገባት ይህ ክፍል ሁለት በንዑስ ርእስ ለዛሬ ከዚህ እንደሚከተለው ተዘረዘረ።
sinod
የሰዎች ድብቅ አመለካከት ወይንም ባህሪ ለዘመናት ግልፅነትን ለማጥፋት ምክንያት  ከሆነ ተሰጦ በአመለካከት የተፀነሰ  ቀናት አስቆጥሮ የሚወለደው ዜግነት አልባ ዘር ይሆንና  ከእኛነት እኔነትን ገንዘብ ያደረገ ብሎም መራርነቱ ለቡዙዎች ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ሀቅ ነው።ለዚህም የሰው ልጅ  ውልደቱም እድገቱም ብቻውን አደለም እና  በሞቱም ጥምረት አያጣውም ።በውልደቱ እንግዴ ልጁ፤በ እድገቱ ወንድም እህቶቹ ብሎም ወላጆች  በሞቱም  በእርሱ የሚጎዱ ሰዎች ሁሉም በአንድም በሌላም በኩል ይኖራሉና  ለዚህ በብልሃት መኖርን የመሰለ የህይወት ትርፍ እንደሌለ ግልፅ ነው ።

ለመንደርደሪያ ታህል ይህን ካልን  ወደተነሳንበት እና ለዚህ ፅሁፍ ምክንያት ስለሆነው ነገር እናንሳ።ቅድስት ሐገራችን  የቡዙ ቤሔረሰቦች ሐገር ሆና  ለቡዙ ዘመናት ብሄረሰቦቿ ጌጦቿ ሆነው ትኖር ነበረም። ትኖራለችም ።

ይህ በእንዲህ ሲኖር ካሉባት ፈተናዎች በተጨማሪ ጎጠኝነት የስርአቱ መለኪያ መስፈሪያ የ ሆነበትን ስርአት  ስታስተናግድ ይኸው 25 አመት ደረሰች ።ይሁንና ይህ ደካማ የፖለቲካ ስርአት ካባውን እንደለበሰ ገራገራውን አልፎ ቤተመቅደስ በመግባቱ  ቅድስት ቤተክርስቲያን  የገፈቱ ቀማሽ ሆና  በገዛ ልጆቿ ልምጭ ስትገረፍ ውላ አደረች። የዚሁ ድንበር የሌሽ ጎጠኝነት ስርዐት ያወቃሉና ችግሩን ይቀርፉታል ተብለው የሚጠበቁት ሰዎች  የችግሩ ባለቤት ሆነው ከነገ ዛሬ መፍትሔ ያመጣሉ ሲባል  ለምእራብዊያን ፍልስፍና እና ለክህደት  ትምህርት ህዝበ ክርስቲያኑን  በማጋለጥ ቤ/ክ ከሐገር ቤት እስከ ውጭ  ሐላፊነት በጎደለው የበላይነት   ለነገ የሚለውን ሳያስቀምጥ  ለማለፍ እሩጫው በርትቷል።በዚህም ይመስላል በሐገረ አሜሪካ የተሰደዱ አባቶቻችን አዋጭ ያልሆነ ነገር በጀመራቸው  ምነው ትህትናውና  ስለቤተክርስቲያን ተብሎ አባቶቻችን የከፈሉትን መስዋትነት  መከፈሉ ቢቀር  እንደ ቡሔ ሆያሁዬ በመንደር አደረጋችሁት? ።በዚህ ምንፍቅና  በልባቸው የሚንቀዋለልውን ጨምሮ ለተሾሙበት ቦታ ብቃታቸው የሚያጠራጥር ታክለውበት  መስፈርቱ የሰፈር ልጅነት በሆነ አካሄድ የጥፋቱ ርዝመት ግርገዳውን አልፎ ሄደ፤የሚለው አስተያየት “የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ” እንዲሉ አበው ያንኑ የተለመደ  ወያኔ ፤ጨዋ  ለማለት የሞኮሩ ወገኖች የበኩላቸውን ብለዋል ።ይሁንና አላማው  እንዲህ ነው ።ሐገር ማለት ከምን ይጀምራል ?ብሔር ማለት ከባለ ሐገርነት የበለጠ የሚያደርገው ምኑ ላይ ነው ።አንድ ዜጋ አስቀድሞ ሊያስብ የሚገባው ልብሱ ክዳኑ ስለሆነችው  ሐገሩ እንጂ  ከማንም ስለማያስበልጠው ብሔሩ ከሆነ ጭፍንነት  እራስን ስለመግዛትና ስለፍቅር  ^የሚያስተምረው  መፅሃፍ ቅዱስ  ሊመልሰው ካልቻለ እኛ የት ነን ?ማነነስ? ።

በዚህ መልኩ ለዘመናት ተከብራ የኖረችውን ቤተክርስቲያን ማፈራረስ ተጠቃሚው ማነው ?ወይስ “ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ  እንዳለችው ዶሮ”እነ አባ ኦርጋን  (መልከፃዲቅ)በምኞት ያጡትን  ስልጣና  በበቀል ለማጠናቀቅ ያላቸውን   ምኞት አጨብጭበን  በመቀበል ከኢትዮጲያዊነት ይልቅ ጎጣችን በልጦብን  የሐይማኖታችንን ነገር በሰፈር ልጅነት ቀየርነው ?ከዘረኝነት በመነጨ ስሜት  ለምን ይህን ተደረገ ለሚለው ጥያቄ እየሱስ ክርስቶስ  ሁሉንስ  ካንድ ወገን  አልነበረም ወይ የሾመው? የሚል ውሃ የማኢቐጥር ምክንያት  ለመስጠት  ተሞክሯል ። እናም አሜሪካውያን  ባለሲኖዶስ  ምን አለበት ጎነደሬ ብቻ ቢሾሙ የታባለበት ሁኔታ አለ። ችግሩ ከክፍለ ሐገሩ ወይም ከሰዎቹ አደለም ።አንደኛ  የቤተክርስቲያኗ ጉዞ ወዴት ነው? ። ሐገር ቤት  ያለው ሁኔታ ሳያንስና  ችግሩ አለማቀፋዊ ሆኖ እያለ እዚህ በነፃነት የሚኖሩ አባቶች ስለ ኢትዮጲያ ሲባል  መካራውንስ ቢታገሱና ቢቆዩ፤ካልሆነም  ደግሞ ወደፊት ሊያድግ  በሚችለው ማንነት ላይ ቢያተኩሩ።ጎጠኝነቱ በፍቅር በሚወደው ወያኔ ላይ አይበቃም ወይ ?አነሱን እየወቀስን እኛ ምን እየሆንን ነው ? ይህን ይህን የመሳሰሉት አባይት ሁነቶች ባለቤት አልባ  መንደር እያደረጉአት ነውና አስብበት ነው ።ይሁንና አንዳዶች ሐሰትን  ለማሳሳት  ሲጠቀሙበት ማየት የተለመደ  ቢሆንም ጌታችን መድሃኒታችን ሐዋሪያት ሲሾም  በአንድ ሐገር ካሉ ከየ ነገዶቹ  ለመሆኑ ከግዚያችሁ ቀንሳችሁ መፅሃፍቱን ብታገላብጡ  ለነገ የሚጠቅማችሁ ይመስለኛል ።ለአብነት ያህል ማወቅ ካለብን  ከዚህ እንደሚከተለው  ለማየት እንሞከር።ከዛ በፊት ግን  ዛሬስ ብፁነታቸው  በግድ ከስልጣናቸው  በመውረዳቸው በመሰደዳቸው ሲኖዶስ ተሰደደ።መቼስ ክፉን ይያዝና አርሳቸው  ወደማይቀረው  አለም ቢጠሩ  ስደተኛው ሲኖዶስ እንደ ተሰደደ አቡነ መልከፃዲቅን ፓትርያርክ አርጎ ይቀጥላል  ወይስ ……….?መልሱን  እና  የቤት ስራውን  ነገን ትዝ ለማይላቸው  ባለቤቶቹ እንተውና  የሐዋርያቱን አሿሿም ለጠቅላላ አውቀት  እንመልከት ።
1.ቅዱስ  ጴጥሮስ -ከቤተ ስሞዖን (በ እናቱ ወገን ) እናቱ ትወደው  ስለነበር  በነገዷ ስም ጠራችው
2.ቅዱስ እንድርያስ -ከቤተ ሮቤል (ባባቱ ወገን )አባቱ ይወደው ነበርና ከነገዱ በተወረሰ ስም ጠራው።
3.ቅዱስ ያቆብ -ከነገደ ሌዊ(በአባቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ -ከነገደ ይሁዳ (በእናቱ)
5ቅዱስ ፊልጶስ -ከነገደ ዛብሎን
7.ቅዱስ ማቴዎስ -ከነገደ  ይሳኮር
8.ቅዱስ ቶማስ -ከነገደ  አሴር
9.ቅዱስ ያዕቆብ  ወልደ  እልፍዮስ -ከነገደ ጋድ
10.ቅዱስ ታዴዎስ -ከነገደ ዮሴፍ
11.ቅዱስ  ስሞኦን ቀነናዊ- ከቤተ ቢንያም
12.ያስቆሮቱ ይሁዳ -ከቤተ ዳን
መሆናቸውን ስላየን  ይህ ለምን ሆነ በማለት “ጎንደሬ ልሁንና ሹሙኝ ” ስንል ርእሱን  ሰጠነው እንጂ ጎንደር የጥበብ ሐገር የሊቃውንቱ መናሐሪያ በመሆኗ ለማሳነስ  ተብሎ የተነገረ አደለም ። ይሁንና ከላይ ስላው የሐዋርያትን ነገር ማውቅ ለሚፈልግ ምንጩ”ቤተክርስቲያንህን  እወቅ  “የሚለው መፅሃፍ ነውና የበለጠ ያብራራላችኋልና   ፈልጋችሁ አንብቡት ።ይህን በዚህ ከቋጭን  የኢ/ኦ/ተ/ቤ መ እመናን  መጪውን የፈተና ዘመን  በእጅጉ ሊያስቡበትና   አሳማ ብሉ፤ ከነጫማችሁ ቤተክርስቲያን  ግቡ፤ቅዱሳን አማላጅነት አያስፈልጋችሁም  እና የመሳሰሉትን ስብከቶች  አስኬማ ባደረገ አባት አንደበት ልትሰሙ ትችላላችሁና   በድርሳነ ሚካኤል  ላይ ታሪኳ  እንደተነገረው  አፎሚያ ዳቢሎስ ሊያሳስታት በመጣ  ግዜ”ንግግርህም ጥሩም አደል መስቀልህስ ከየት አለ በእውነቱ አንተ ከመላእክት  ወገን  ከሆንክ…. “እንዳለችው ትምህርቱን ሁሉ መመርመር የግድ የሚልበት እና እነ አባ እከሌ ይህን አሉ ሳይሆን “አውነት ምን ብሎአል?”የሚለው ነገር ላይ የምናተኩርበት  ሰአቱ አሁን መሆኑን እንድናስብ ግድ ነው ። በርግጥ አውቆ የተኛን ቢጠሩት አይሰማምና  ጎጠኝነት አናቱ ላይ ለወጣ ማህበረሰብ  ከማንም  በላይ  የሚያሳስበው  ምድራዊው ነውና  ከሞትህ ትማራለህ ከማለት ያለፈ አስተምሮ ሊኖር አይችልም ። ስለሁሉም መፅሃፍ ቅዱሳችን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2ተኛ  ከቁጥር 1 አስከ 18 አንድህ ይላል”
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ።
ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።
የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።
ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።
ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዓት አልሄድንምና፤
ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።
ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።
ደግሞ ከእናንተ ጋር ፦ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና።
ሥራ ከቶ ሳይሠሩ፥ በሰው ነገር እየገቡ፥ ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና።
እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን።
እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።
በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፥ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።
ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።
የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
በመቀጠልም ምሳሌ 18ቁ 1″  መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።
ይቆየን

No comments:

Post a Comment

wanted officials