Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 21, 2016

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከህዝቡ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተባለ

የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት እንደገለጹት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ በአጠቃላይ የታሰሩትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ጉዳይ የሚከታተሉ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ኮሎኔሉ ወደ ትግራይ ተላልፈው እንደማይሰጡ እንዲሁም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ኮሎኔሉና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት ለሽማግሌዎች ተመልሰው እንደሚሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ኮሎኔሉ ራሳቸው ሽማግሌዎች በተስማሙት መሰረት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የተናገሩት የኮሚቴ አባላቱ፣ አሁን ግን ኮሎኔሉ ጎንደር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ሽማግሌዎቹ ዛሬ ከኮሎኔሉ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ በወልቃይት ጠገዴና በጎንደር ህዝብ ላይ ጉዳት ያደረሱትን በህግ ለመክሰስ፣ ታፍነው የተወሰዱ የኮሚቴው አባላት ለሽማግሌዎቹ ተመልሰው እንዲሰጡ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ኮሎኔል ዘውዱ ከፍተኛ ጀብዱ መፈጸማቸውን የሚያወሱት የኮሚቴው አባላት፣ ኮሎኔሉ በሰላም ከተኙበት ለማፈን ሙከራ ያደረገው የህወሃት የሽፍታና ተላላኪ ቡድን እርሳቸውን ለመክሰስ ምንም የሞራልም የህግ ልእልናም ስለሌለው የጎንደርም፣ የአማራም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ሃይል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማድረግ አለበት ይላሉ። ስምምነቱ ኮሎኔሉንና የኮሚቴ አባላቱን መልሶ ለሽማግሌዎች ለማስረከብ በመሆኑ ስምምነቱ መፈጸም አለበት ብለዋል
በበየዳ፣ በዳንሻ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት ህዝባዊ ተቃውሞች ከመልካም አስተዳደርና ገዢው ፓርቲ ከሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲ ጋር እንደሚያያዝ የኮሚቴው አባሉ ተናግረዋል። 

No comments:

Post a Comment

wanted officials