Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 11, 2016

አዲስ አበባ ለአስረኛ ጊዜ ማስተር ፕላን ተዘጋጀላት ተባለ


ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ እንደዘገበው  ወያኔ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ዘጠኝ ጊዜ ማስነደፉ ይታወቃል፡፡ በሰኔ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ይኸው ለአስረኛ ጊዜ የተነደፈው ፕላን ይፋ ሆኗል፡፡ ይህን ፕላን ለመንደፍ ያስገደደው ለአዲስ አበባ አጎራባች የሆኑ ከተሞችንና የእርሻ መሬቶችን ወደ ከተማዋ ለመቀላቀል የተነደፈው ፕላን በኦሮሞ ተማሪዎችና ወጣቶች ብርቱ ተቃውሞ መገታት በመቻሉ ነው፡፡
የአዲስ አበባ የመሬት ስፋት 54 ሺ ሄክታር በመሆኑና ወደ ጎን እየተለጠጠ ለመሄድ እንደማይችልም ተገልጿል፡፡ በዚህ ሳቢያ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ መሀል አዲስ አበባን የማፍረስ ዘመቻ እንደሚጀመር ይፋ ተደርጓል፡፡ ወያኔ አዲስ አበባን በትግራይ ተወላጆች ለመሙላት ካለው መሰሪ ዓላማ በመነሳት በመሀል ከተማ የሚኖረውን ዜጋ ከከተማዋ ገፍቶ ለማስወጣት የታለመ መሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡
ለዚህ ማስተር ፕላን ማስፈጸሚያ 290 ቢሊዮን እንደሚስፈልግ የተጠቆመ ሲሆን በቅድሚያ አለሁ ከሚል አበዳሪ ድርጅት ለመበደር እቅድ መያዙንም ለከንቲባው ቅርብ የሆኑ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ፕላን መሰረት ብሔራዊ ቤተ መንግሰት፣ ግዮን ሆቴል፣ መከላከያ ሚንቴር ሙዚየምና መናፈሻ ይሆናሉ፡፡ የወያኔ ነገር የቧይ ካብ እንደሆነ የሚያስረዱ ወገኖች እንደሚሉት በአስራ ዘጠኝ ሰማንያዎቹ መጨረሻ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረው ተፈራ ዋልዋና የመከላከያ ሚንትር የነበረው ታምራት ላይኔ መከላከያ ሚንስቴር እንዲፈርስና በምትኩ ሌላ እንደሚሰራ ተፈራርመው እንደ ነበር ያስታውሳሉ፡፡ ወያኔ ቆሞም ሆነ ተቀምጦ የሚያልመው ብድር ማግኛ መንገድ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials