Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 21, 2016

ሰበር ዜና! ቤታቸው በክረምት የሚፈርስባቸው ወገኖች በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እናደርጋለን አሉ፡፡

ሰሞኑን በቃሊቲ ገብርኤል ወረዳ.07 ቀበሌ10/11-ልዩ ስሙ ጨሬ ሰፈር በመባል የሚታወቀው ኣካባቢ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ በአፍራሽ ግብረ ሃይል ምልክት ተደርጎባቸው በሁለት ቀን አፍረስው ካልጨረሱ በዶዘር ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው፡፡ በሁኔታው የተቆጡ ነዋሪዎች መንግስት በዜጎቹ የሚፈጽመው ጭካኔ እንግዲህ በቃ,ሞት ተፈርቶ ውርደት መቀበል አንችልም እያሉ ይገኛል፡፡ በዚህ ክረምት የት እንሄዳለን በማለት የተቆጡ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡም እንዳሰብ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ ነዋሪ ሲናገሩ በቅርቡ ወረገኑ በርካታ ሰዎች ሜዳ ላይ ወደቁ በን/ስ/ላ ቀበሌ01 ቀርሳ ኮንቶማ ማንጎ ከ20 ሺህ በላይ ቤቶች አፈረሱ ሕጻናት አረጋዊያን ያለ መጠለያ በሜዳ ላይ በዚህ ክረምት ለጎርፍና ለጅብ ቀለብ ተሰጥተዋል፡፡ መንግስት የሌለው ሕዝብ መሆናችን በደንብ አይተናል፡፡ እነሱ ከበርሃ አዲስ አበባ በኮንጎ መጥተው ባለ ፎቅ ሲሆኑ እኛ ተወልደን ባደግንበት ምድር እንዴት ቤት እናጣለን? በማለት በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ መኖር ሞታችን ይመረጣል የሚሉት ሌላው ነዋሪ ከዚህ በላይ ሞት ምን አለ? ሁል ጊዜ ቤታችን አፈረሱት በማለት ማልቀስ አንፈልግም የጎንደር ሕዝብ አሳይቶናል በቃ..ሰልፍ እንወጣለን መንዱን በተቃውሞ ይዘጋል ሲሉ ተናግረዋል፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials