ከጎንደር ከተማ 42ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ማክሰኝት ከተማ ደማቅ ሰልፍ ተካሂዷል ።
የሰልፉ ዓላማ በከተማዋ የሚኖሩ የመንግሥት ሰራተኞች እና ነጋዴዎች ፣ ሾፌሮች ፣ አርሶአደሮችን ያሳተፈ ሲሆን በመኖሪያ ቤት እጦት ምክንያት በማህበር ተደራጁ ይሰጣችኋል እየተባለ ሁለተኛ ዓመት ተቆጠረ ፡ ከዚህ በፊት የወረዳው አመራር የነበረበት ያለምንም እንከን ከተመራ/ከተሰጣቸው በሇላ አሁን በጥያቄ ላይ ያለው በማህበር ደረጃ ከ60በላይ ሲሆን የማህበሩ አባላት ደግሞ ወደ 2000አካባቢ ከላይ እንደጠቀስኩት ሁሉንም አቀፍ ማህበረሰብ ያካተተ ሲሆን በተደጋጋሚ የይሰጠን ጥያቄው ቢጠየቅም ከወረዳ እስከ ክልል አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም በመሆኑም በዚህ የተቆጣው ህዝብ ፈቃድ ሳያስፈልግ ሰልፍ በመውጣት ለ30ደቂቃ ያህል መንገዶች ተዘግው መኪና ማለፍ አልቻለም በዚህም የተነሣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ እባካችሁ 30ደቂቃ ስጡን ከዚያ የዞኑን ምክትል አስተዳደር እና የፀጥታ አስተዳደር የሆኑት አቶ መኮነንን እናመጣለን መልስ ይሰጣሉ በማለት ለማረጋጋት የሞከረ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ መልሳችሁ መንገድ መዝጋት ትችላላችሁ ካሉ በሗላ ሰውየው ከ30ደቂቃ በሗላ በሶስት ወሮበሎች ጥበቃ ታጅቦ መጣና ሀሳቦችን ብዙም ሳይቀበል እስከ ሐምሌ 30 አጥጋቢ ምላሽ እንሰጣለን አሉና በ24እናበ25ትልቅ ስራ ስላብን አሉ ለመግለፅ ባይደፍርም በፊታችን እሁድ የሚካሄደውን ሰልፍ መሆኑን ነው ። ሌላው ግን አንድ ሳልገልጽ የማላልፈው ነገር ደግሞ የወያኔ ታጋይ የነበረው አቶ አምሳሉ ይባላል ከ9ዓመት በላይ አብሯቸው እንደ ታገለ ከገለፀ በሗላ እኔ የታገልኩት ለዚህ ስርዓት ከሆነ ምነው በዛ ጊዜ ሞቼ ቢሆን በማለት የአብዛኛውን ልብ በሚሰብር መልኩ በምሬት ተናግረዋል ። ያም ሆነ ይህ እሁድ ጎንደር እንገኛለን ቸር እንሰንብት ድል ለሰፊው ህዝብ!!!
No comments:
Post a Comment