Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 8, 2016

የሰይፉ ፋንታሁን የሸገር ቆይታ እስከ መስከረም ተራዘመ (አላሙዲ ለነሰይፉ ባንክ ያስገቡትን ገንዘብ አወጡት)

ሰይፉ ፋንታሁን በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የሚያቀርበውን ‹‹ታዲያስ አዲስ›› የሬዲዮ ፕሮግራም ሰኔ 30 እንዲያቆም ከጣቢያው ደብዳቤ ደርሶት ነበር፡፡ ይሁንና እንደምንጮችችን ገለፃ ይህ ውሳኔ ተቀልብሶ እስከ መስከረም ፕሮግራሙን እያቀረበ እንዲቀጥል ተራዝሞለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለቤተሰብ ጉዳይ በአሜሪካ የምትገኘው የሸገር ሀላፊ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ የሰይፉን ቆይታ ያራዘመችው ያቀረበው ምክንያት አሳማኝ ሆኖ ስላገኘችው ነው ተብሏል፡፡
Fantahun Seifu and Mahder Assefa
እንደሚታወቀው ሰይፉ ከሸገር የሚለቀው የራሱን የሬዲዮ ጣቢያ ስለሚጀምር ነው፡፡ ‹‹ዋን ላቭ›› የተሰኘውና በመስከረም ስርጭት እንደሚጀምር የተነገረለት ይህ ጣቢያ በሰይፉ፤ በሰራዊት ፍቅሬና በአርቲስት ማህደር አሰፋ(በወንድሟ በኩል) የተቋቋመ ሲሆን የገንዘቡ ምንጭ ደግሞ ሼህ መሐመድ አልአሙዲ ናቸው፡፡
አልአሙዲ ይህ የሬዲዮ ጣቢያ እንዲቋቋም የሚያስፈልገውን የ8 ሚሊዮን ብር ካፒታል በእነሰይፉ ስም አስገብተው የንግድ ፈቃዱ ከተሰጣቸው በኋላ ብሩን መልሰው ወስደውታል፡፡ ይሁንና ማንኛውንም ለጣቢያውና ለስቱዲዮ ማቋቋሚያ የሚያስፈልገውን ወጪ እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡ የገቡትን ቃል እስካሁን ለማሳካት እንዳልቻሉ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ለሬዲዮ ጣቢያው እስካሁን ቢሮ ለመከራየት እንኳ እንዳልቻሉ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ለስቱዲዮ የሚሆኑ እቃዎችን ለመግዛት ከአንድ ድርጅት ጋር ተዋውለው ድርጅቱ እቃዎቹን ቢያስመጣም ከፍለው ለመውሰድ አልቻሉም፡፡ አልአሙዲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህደር ጋር እየተደባበሩ መምጣታቸው ቃል የገቡትን የሬዲዮ ጉዳይ ላለማሟላት ወደኋላ እንዲሉ እድርጓቸዋል የሚሉ አሉ፡፡
ይህን ምስጢር የተረዳችው አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ የሰይፉን ቆይታ እስከመስከረም አራዝማዋለች ብለዋል ምንጮቻችን፡፡
(በዋን ላቭ ሬዲዮ የአርቲስት ማህደር ወንድም ከ60 ፐርሰንት በላይ ድርሻ አለው)

No comments:

Post a Comment

wanted officials