Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 11, 2016

የውጪ ምንዛሬ እጦት የወያኔን አከርካሪ እየሰባበረው መሆኑ የተሰማ ሲሆን የዲያስፖራው ጫና በርትቷል።



የውጪ ምንዛሬ እጦት የወያኔን አከርካሪ እየሰባበረው መሆኑ የተሰማ ሲሆን የዲያስፖራው ጫና በርትቷል።




የውጪ ምንዛሬ እጦት የወያኔን አከርካሪ እየሰባበረው መሆኑ የተሰማ ሲሆን የዲያስፖራው ጫና በርትቷል። – በሃገር ውስጥ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ወያኔ እመራዋለሁ በሚለው የተጭበረበረ ኢኮኖሚ ላይነሳ መኮታኮቱን ምንጮች ይናገራሉ።ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት የሚልኩትን ገንዘብ ተገን በማድረግ ኢኮኖሚውን ደግፎ ያቆየወ ወያኔ ባለፈው አመት ብቻ የነዳጅ ዋጋ መቀነስና ዲያስፖራው ለቤተሰቡ ከሚልከው ገንዘብ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮችን በማፈስ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት አውሎታል። ዲያስፖራው የሚልከውን ገንዘብ በማቆም\በመቀነስ ወያኔን ክፉኛ እየቀጣው መሆኑ ምን ያህል ባለጡንቻ ዲያስፖራ እንዳለን ያሳያልና መቀጠል አለብን በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ፍርፋሪ ዶላር በባንክ አንላክ።ሌላው የሃገር ውስጥ ታዋቂ ነጋዴዎችን ጨምሮ የወያኔ ባላባቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያሸሹ መሆኑ ነው፥፥የተረፈ ካለ ደሞ ወደ ባንክ ከመውሰድ ይልቅ ቤጅ መያዝ እየተመረጠ መቷል፥፥አገር ውስጥ ደሞ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጪ አገር መላክ እየተለመደ መቷል፥፥ምንሊክ ሳልሳዊ አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ብለዋል የስርኣቱ ታማኞች።ይህ የሚያመለክተው ዜጎች በፖለቲካው ጉዞ ላይ እምነት እንዳሌላቸው ሲሆን እየተሽመደመደ እና እየደቀቀ ያለው የፖለቲካ ስራቲ ምንም ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉ ሰዎች በወንጀለኝነት ሳይሆን በአስተሳሰባቸው ወህኒ መውረዳቸው የፈጠረው ስጋት ነው።


የስርኣቱ ቅርብ ምንጮች በሃገር ውስጥ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በመሽመድመዱ ወያኔ ወገቡ መቆረጡን እና መምራት አለመቻሉን በለሆሳስ በመተንፈስ ኢኮኖሚው መንኮታኮቱን ሲናገሩ የንግድ ስራዎች ከፓርቲ ድርጅቶች ውጭ በጣም ተዳክመው እና ሞተው ያሉ ሲሆን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ጭራሽ ገደል መግባታቸውን እና ደንበኞች በባንኮች ላይ ያላቸው አመኔታ በመጥፋቱ ግንኙነቶች መልፈስፈሳቸው በይበልጥ ለግል ባንኮች መዳከም ምክንያት ሆነዋል ሲሉ ይህ ደግሞ አሉ የገንዝብ እንቅስቃሴውን ገድሎታል፥ በጣም ድብን ያለ እውነት ነው።በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡ ብለውም አክለው አስቀምጠዋል።

ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም። በኢንቨስትመንት እንሰማራለን ብለው የመጡ የውጭው አለም ሰዎች በቢሮክራሲው መንተክተክ የተነሳ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ትብብር ማግኘት አለመቻላቸውን፣ የውጪ ምንዛሬ ኣለመኖር ሙስናውን የግልጽ ገበያ ዘረፋውን ጨምሮ መስራት እንዳልቻሉከመናገራቸውም በላይ የጀመሩት ኢንቨስትመት እንደሚቋረጥ የወያነ ባለስልጣናት እንደሚያስቆሟቸው እና ለምን ሲሉ መልስ የሚሰጣቸው አከል እንደሌለ እና ጨረታ ካሸነፉ በኋላ እንደሚሰረዝ ለማን እንደሚሰጥ እንደማያውቁ አማረው እየተናገሩ ነው፥ኣገር ጥለው የተበደሩትን ሳይከፍሉ እየሸሹ ሲሆን በኣዋሳና ድሬደዋ ያሉ የለስላሳ ምጣጥ ፋብሪካዎች ተዘግተዋል። የተለያዩ ይውጪ ኢንቨስተሮች ድርጅቶች በልማት ባንክ በኩል ለሽያጭ በጨረታ እየቀረቡ ነው።እንደ ምንጮቹ ዘገባ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials