በጎንደር ሕዝባዊው አመጽ የበርካታ ጀግኖችን ሕይወትን እያስቀጠፈ ነው:: ሕወሓት መራሹ መንግስት በጥይት የቆላቸውን ጀግኖች ፎቶግራፋቸውን በማሰባሰብ እነዚህን ጀግኖች ሕዝብ እንዲያውቃቸው እንሞክራለን:: በትናንትናው ዕለት ሕይወታቸውን ለዚህ ትግል ከከፈሉት መካከል በፎቶ ግራፉ ላይ የምትመለከቱት የአርማጭሆው ተወላጅ ሰጠኝ ባብል ይገኝበታል:: ሰጠኝ ወልቃይት አማራ እንጂ ትግራይ አይደለም; የአማራ ማንነታችን ይመለስ በሚል ጠመንጃ ካነሱ የጎንደር ተወላጆች መካከል አንዱ ነው:: ሰጠኝ በሕወሓት ወታደሮች በጥይት ተደብድቦ ሕይወቱ አልፏል:: አርበኛውን ተዋወቁት::

No comments:
Post a Comment